ሚዲያ

የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በፖሊስ መወሰዱ ተነገረ

የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው ዛሬ ረቡዕ ጠዋት በአዲስ አበባ ከሚገኘው መስሪያ ቤቱ በፖሊሶች ተይዞ መወሰዱን የስራ ባልደረቦቹ ተናገሩ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የደንብ ልብስ የለበሱት ፖሊሶች፤ ሶስት ላፕቶፖችን ጨምሮ መገናኛ ብዙሃኑ ለስራ የሚጠቀምባቸውን ቁሳቁሶችን ከጋዜጠኛው ጋር አብረው መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።  ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀ አንድ የአውሎ ሚዲያ ባልደረባ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደገለጸው፤ ዋና አዘጋጁ የተያዘው...

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የጋዜጠኞች የጉዞ ክልከላን በተመለከተ “መረጃ አልነበረኝም” አለ

በተስፋለም ወልደየስ ከነገ በስቲያ በትግራይ የሚካሄደውን ምርጫን ለመዘገብ፤ ዛሬ ወደ መቀሌ ሊጓዙ የነበሩ ጋዜጠኞች ከአውሮፕላን ጣቢያ እንዲመለሱ መደረጉን በተመለከተ...

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ምክትላቸው ከኃላፊነታቸው ተነሱ

በተስፋለም ወልደየስ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቀለ ሙለታ እና ምክትላቸው አቶ ብሩክ ከበደ ከትላንት ሰኞ ነሐሴ...

የወላይታ የማህበረሰብ ሬድዮ ወደ ስርጭት ተመለሰ

በጸጥታ ኃይሎች ትዕዛዝ ካለፈው አርብ ነሐሴ 8፤ 2012 ጀምሮ ስርጭቱን አቋርጦ የነበረው የወላይታ ዎጌታ የማህበረሰብ ራዲዮ ጣቢያ ከዛሬ ሰኞ ማለዳ ጀምሮ መደበኛ ዝግጅቱን ማስተላለፍ ጀመረ። ጣቢያው ስራውን የጀመረው የጸጥታ ሁኔታ እየተቆጣጠረ ከሚገኘው ኮማንድ ፖስት ኃላፊዎች ጋር ከተደረገ ውይይት በኋላ ነው ተብሏል። በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በተደረገው ውይይት የራዲዮ...

የወላይታ የማህበረሰብ ሬድዮ ስርጭት በጸጥታ ኃይሎች ትዕዛዝ እንዲቋረጥ ተደረገ

በተስፋለም ወልደየስ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የዎጌታ የማህበረሰብ ራዲዮ ጣቢያ ስርጭት ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በጸጥታ ኃይሎች ትዕዛዝ እንዲቋረጥ መደረጉን የጣቢያው ጋዜጠኞች አስታወቁ። ትዕዛዙን የሰጡት፤ ጣቢያው ወደሚገኝበት ግቢ የገቡ የታጠቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሆናቸውንም ተናግረዋል።  ለደህነንታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የጣቢያው...

የOMN ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ውሎ

በተስፋለም ወልደየስ ፖሊስ በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች ላይ ያቀረበው ተጨማሪ የምርምራ ጊዜ በፍርድ ቤት ተፈቀደለት። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄም ውድቅ ተደርጓል።    የምርምራ ጊዜውን የፈቀደው እና የዋስትና መብቱን የከለከለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት...

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ተከሰሰ

በተስፋለም ወልደየስ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በቅርቡ የጸደቀውን የሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ ዛሬ፤ ማክሰኞ ሚያዝያ 13፤ ክስ እንደተመሰረተበት የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ። የያየሰው ጠበቃ በበኩላቸው ጋዜጠኛው ዛሬ ወደ ፍርድ ቤት ቢወሰድም ችሎት ፊት አለመቅረቡን እና ክሱም እንዳልደረሰው ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተናግረዋል። 

የፌስቡክ የሶስተኛ ወገን መረጃ የማጣራት ስራ በኢትዮጵያ ሊጀመር ነው

ዓለም አቀፉ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ፌስቡክ በሌሎች አፍሪካ ሀገራት እያካሄደ የሚገኘውን በሶስተኛ ወገን የሚካሄድ የመረጃ የማጣራት ስራ በኢትዮጵያም ሊጀምር መሆኑን ዛሬ አስታወቀ። መረጃ የማጣራት ስራው የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ትክክለኛ ዜናዎችን እንዲያገኙ ከማገዙም ባሻገር በገጹ ላይ የሚስተዋለውን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሎለታል።

ለጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ለሁለተኛ ጊዜ ዋስትና ተፈቀደ

በተስፋለም ወልደየስ በ“ሽብር ማነሳሳት” ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር እንዲቆይ የተደረገው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የ30 ሺህ ብር ዋስትና ተፈቀደለት። ለጋዜጠኛው ዛሬ ሰኞ፤ ሚያዝያ 12፤ 2012 ዋስትናውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ጋዜጠኛ ያየሰው በመጀመሪያ በቁጥጥር ስር የዋለው...

ኢትዮጵያዊው ፎቶ ጋዜጠኛ ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ

ኢትዮጵያዊው ፎቶ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አየነ በዘንድሮው የ“ወርልድ ፕሬስ ፎቶ” ዓለም አቀፍ ሽልማት ውድድር በአንድ ምድብ አሸነፈ። ሙሉጌታ ሽልማቱን ያሸነፈው ባለፈው ዓመት ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን በተመለከቱ የፎቶግራፍ ስብስቦቹ ነው።  ሙሉጌታ ስመ ጥር ለሆነው “ወርልድ ፕሬስ ፎቶ” ሽልማት የዘንድሮ ውድድር የታጨው በሶስት...

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶችን በቀጥታ ማሰራጨት ጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያለው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤ. ኤም. ኤን) ቴሌቪዥን ጣቢያ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶችን በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ጀመረ፡፡ ጣቢያው ስርጭቱን የጀመረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት በቤተ እምነቶች የሚደረጉ የሰዎች መሰባሰቦችን ለማስቀረት እንደሆነ የጣቢያው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የጣቢያው ከፍተኛ አመራሮች...

በጋዜጠኛ ያየሰው ጉዳይ የ6 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ

በሐይማኖት አሸናፊ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ ጠዋት ቀርበው የነበሩት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ ቀሪ ምርመራዎችን ለማካሄድ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀው ፖሊስ ስድስት ቀን ተፈቀደለት። አርብ መጋቢት 18፤ 2012 በቅርብ ዘመዳቸው መኖሪያ ቤት በቁጥጥር ስር የዋሉት ያየሰው ከመታሰራቸው አንድ ቀን በፊት "ኢትዮ ፎረም" በተሰኘው የዩቲዩብ ቻናላቸው ያሰራጩት...