ምርጫ 2013

አራት ዓለም አቀፍ ተቋማት የምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚልኩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

በቅድስት ሙላቱ  የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ አራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ለመጪው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢዎችን ለመላክ መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ ገለጹ። ቃል አቃባዩ ዛሬ ማክሰኞ በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ምርጫውን በዋናነት ይታዘባል ተብሎ ከሚጠበቀው የአፍሪካ ህብረት በተጨማሪ ሁለት የአሜሪካ እና አንድ የሩሲያ ተቋማት ታዛቢዎችን ወደ ኢትዮጵያ ይልካሉ።  በአሜሪካ በኩል ምርጫውን ለመታዘብ ፍቃደኝነታቸውን የገለጹት ኢንተርናሽናል ሪፐብሊካን ኢንስቲትዩት (IRI)...

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ እና የአፋር ህዝብ ፓርቲ ለምርጫ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) እና የአፋር ህዝብ ፓርቲ ለመጪው ምርጫ በጋራ ለመስራት ስምምነት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 3 ተፈራረሙ። በስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የአፋር ህዝብ...

የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ላለመላክ ያስተላለፈውን ውሳኔ መልሶ እንዲያጤን ተጠየቀ

በቅድስት ሙላቱ  የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላለመታዘብ ያስተላለፈውን ውሳኔ መልሶ እንዲያጤነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠየቀ። ምክር ቤቱ፤ የአውሮፓ ህብረት...

የመራጮች ምዝገባ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባን ለሶስተኛ ጊዜ አራዘመ። የመራጮች ምዘገባ ዛሬ ይጠናቀቅባቸው በነበሩ በሰባት ክልሎች እና በሁለት የከተማ መስተዳድሮች ቀነ ገደቡ ለተጨማሪ አንድ ሳምንት መራዘሙን ቦርዱ ዛሬ አስታውቋል።  ምርጫ ቦርድ በመጀመሪያ ባወጣው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የመራጮች ምዝገባን ለማከናወን አቅዶ የነበረው ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21፤ 2013 ነበር። ቦርዱ የምርጫ...

የመራጮች ምዝገባ እስካሁን ባልተጀመረባቸው ቦታዎች ምዝገባ “በልዩ ሁኔታ” ሊደረግ ነው

በተስፋለም ወልደየስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ እስካሁን ባልተጀመረባቸው ቦታዎች ምዝገባው “በልዩ ሁኔታ” እንዲከናወን ውሳኔ አሳለፈ። የመራጮች ምዝገባ በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን ውሳኔ የተላለፈላቸው ቦታዎች በኦሮሚያ፣ አማራ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚገኙ ናቸው።  ምርጫ ቦርድ ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በሶስቱ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ቦታዎች የመራጮች ምዝገባ የሚደረገው ከመጪው ሚያዝያ...

የአውሮፓ ህብረት ለመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ ታዛቢዎች እንደማይልክ አስታወቀ

የአውሮፓ ህብረት ለስድስተኛው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ታዛቢ ለመላክ የያዘውን እቅድ ሰረዘ። ህብረቱ ግንቦት 28፤ 2013 ለሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ ታዛቢዎች ለመላክ በቁልፍ መለኪያዎች ረገድ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ከስምምነት መድረስ እንዳልቻለ ትናንት ሰኞ ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።  በ74 አመቱ ስፔናዊ ጆሴፕ ቦሬል የሚመራው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ቢሮ ባወጣው መግለጫ እንዳለው “ሁኔታዎች...

የመራጮች ምዝገባ ተራዘመ

በተስፋለም ወልደየስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሶማሌ እና አፋር ውጪ ባሉ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ ለሁለት ሳምንት እንዲራዘም ውሳኔ አሳለፈ። የመራጮች ምዝገባ “እጅግ ዘግይቶ ተጀምሮባቸዋል” ባላቸው በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ደግሞ ምዝገባው ለሶስት ሳምንታት እንደሚራዘምም ገልጿል።  ቦርዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በሶስት ምክንያቶች መሆኑን ዛሬ አርብ ምሽቱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ቦርዱ...

የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ በመቃወም ለፓርላማ አቤቱታ ሊያስገባ ነው

በቅድስት ሙላቱ የሐረሪ ብሔረሰብ አባላት የምርጫ ተሳትፎን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈውን ውሳኔ የተቃወመው የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ጉባኤ፤ ጉዳዩን ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊወስደው ነው። ጉባኤው የቦርዱን ውሳኔ “በአጭር ጊዜ ለማስቀየር ያስችላሉ” ያላቸውን ህጋዊ አማራጮች በሙሉ ጎን ለጎን እንደሚያስኬድ አስታውቋል።  የሐረሪ ክልል ከፍተኛ የሕግ አውጪ አካል በሆነው የክልሉ ምክር...

ኢዜማ ለአዲስ አበባ ከተማ ያዘጋጀውን የምርጫ ማኒፌስቶ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ለአዲስ አበባ ከተማ ያዘጋጀውን የምርጫ ማኒፌስቶ ዛሬ ረቡዕ ይፋ አድርጓል። “የቃል ኪዳን ሰነድ” ስያሜ በተሰጠው በዚህ ማኒፌስቶ፤ ፓርቲው ሊያሳካቸው ያቀዳቸው 138 ቁልፍ ግቦች ተካትተውበታል።  በአስራ አምስት ክፍሎች ተከፋፍሎ በተዘጋጀው ሰነድ፤ የአዲስ አበባ ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ፣ የመኖሪያ ቤቶች እጥረት መቅረፍ፣ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር መዘርጋት፣ የከተማዋን...

መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የመደበው 98 ሚሊዮን ብር መከፋፈል ሊጀምር ነው

በተስፋለም ወልደየስመንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲከፋፈል በዚህ አመት ከመደበው 98 ሚሊዮን ብር ውስጥ፤ የተወሰነው መጠን በሚቀጥለው ሳምንት ለፖለቲካ ፓርቲዎች መከፋፈል ሊጀመር ነው። ለፓርቲዎች የሚሰጠው ገንዘብ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት እንዲከፋፈል በቀመር አማካኝነት የተደለደለ ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የክፍፍል ቀመር መሰረት መንግስት ለፓርቲዎች ከሚመድበው ገንዘብ ውስጥ 25 በመቶ ያህሉ፤...

በመተከል፣ ካማሺ እና ወለጋ ዞኖች ለመራጮች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ስልጠና ማድረግ አልተቻለም – ምርጫ ቦርድ

በተስፋለም ወልደየስ  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጸጥታ ችግር በሚስተዋልባቸው ሁለት ዞኖች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በወለጋ አካባቢ ባሉ አራት ዞኖች ለመራጮች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ስልጠና መስጠት አለመቻሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቦርዱ ይህን የገለጸው የመራጮች ምዝገባ ሂደትን እና ሌሎችንም ጉዳዮች በተመለከተ ዛሬ ቅዳሜ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በአዲስ አበባ ባደረገው ውይይት ላይ ነው።  የምርጫ...

ኢዜማ ከየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ በላቀ ችግር የገጠመው በኦሮሚያ ክልል ነው- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ከየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ በላቀ ብዙ ችግር የገጠመው በኦሮሚያ ክልል መሆኑን መሪው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። በክልሉ ያሉ የፓርቲው አባላት መታሰር፣ መሰደድ እና የጽህፈት ቤቶች መዘጋት ባለፉት ሁለት ወራት ይበልጥ ተባብሷል ብለዋል።     ፕሮፌሰር ብርሃኑ ይህን ያሉት ፓርቲያቸው በአዳማ ከተማ ዛሬ እሁድ ረፋዱን በጠራው...

የምርጫ ክርክር ለማዘጋጀት 11 ተቋማት የምርጫ ቦርድን ይሁንታ አገኙ

በተስፋለም ወልደየስ  የምርጫ ክርክር ለማዘጋጀት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፍላጎታቸውን በጹሁፍ ካቀረቡ ተቋማት መካከል አስራ አንዱ የቦርዱን ይሁንታ አገኙ። ምርጫ ቦርድ ዛሬ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ግምገማ ካቀረባቸው ከእነዚህ ተቋማት መካከል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የባለሙያዎች ማህበራት እና የብዙሃን መገናኛዎች ይገኙበታል።  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ እንደተናገሩት 23 ድርጅቶች የምርጫ...

በመጪው ምርጫ ለመወዳደር ከስምንት ሺህ በላይ ዕጩዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

በግንቦት ወር መጨረሻ ለሚደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ በፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ 8,209 ዕጩዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ። ቦርዱ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 2 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው 125 የግል ተወዳዳሪዎችም በምርጫው ለመወዳደር በዕጩነት ተመዝግበዋል።   የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶች ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች መካከል 47ቱ ዕጩዎችን ማስመዝገባቸውን ቦርዱ በመግለጫው ጠቅሷል። አራት...

ኦነግ በመጪው ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታወቀ

በተስፋለም ወልደየስ  በዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻ በሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታወቀ። መጪውን ምርጫ “ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ” ሲል የጠራው ኦነግ፤ "በምርጫ መሳተፍ አለመቻሌን ስገልጽ ሀዘን ይሰማኛል” ብሏል።   ኦነግ ሰኞ የካቲት 29 ለሊት በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ  ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ግንባሩ ከዚህ ውሳኔ ላይ...

በየምርጫ ክልሎቹ የሚወዳደሩ ዕጩዎች ማንነት ይፋ ተደረገ

የፎቶ ዘገባ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ ፓርቲያቸውን ወክለው አሊያም በግል በየምርጫ ክልሎቹ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ማንነት ዛሬ ይፋ አድርጓል። በዕጩዎች መመዝገቢያ ጽህፈት ቤቶች ፊት ለፊት በተለጠፉት የቦርዱ የማሳወቂያ ቅጾች፤ የምርጫ ተወዳዳሪዎችን ሙሉ ስም፣ የመወዳደሪያ ምልክታቸውን፣ ማንን ወክለው በዕጩነት እንደቀረቡ፣ ዕድሜያቸውን፣ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ እንዲሁም የትምህርት ደረጃቸውን ዝርዝር...

የመራጮች ምዝገባ ተራዘመ

ምስላዊ መረጃ፦ ዛሬ የካቲት 22 ሊጀመር ቀን ተቆርጦለት የነበረውን የመራጮች ምዝገባ፤ ወደ ቀጣዩ ወር መጋቢት አጋማሽ መዛወሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ ለቀኑ መራዘም በምክንያትነት ከጠቀሳቸው ውስጥ የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤቶችን ለመክፈት በክልል መንግስታት በኩል የታየው ዳተኝነት፣ የዕጩዎች ምዝገባ መራዘም እና የምርጫ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የገጠመው ተግዳሮት ይገኙባቸዋል። በተሻሻለው...

በእስር ቤት ያሉ ፖለቲከኞች ለምርጫ በዕጩነት መቅረብ እንደማይችሉ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

በተስፋለም ወልደየስ  በእስር ቤት ያሉ ፖለቲከኞች ለምርጫ በዕጩነት መቅረብ እንደማይችሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቦርዱ ይህን የገለጸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በእስር ላይ ያሉ አባላቱ በመጪው ምርጫ ዕጩ ሆነው መቅረብ ይችሉ እንደው ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። ጥያቄው የቀረበው ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ማክሰኞ የካቲት 16 ባደረገው ስብሰባ ላይ ነበር።በዳውድ ኢብሳ...