ሰሞነኛ ጉዳዮች

የፓርላማው ኮሚቴ ስለ መጅሊስ አዋጅ ምን ተወያየ?

9 ደቂቃ ንባብ
በተስፋለም ወልደየስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠ ወዲህ መደበኛ ስብሰባዎችን ማስተናገድ ያቆመው ዕድሜ ጠገቡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋናው አዳራሽ፤ ዕድሜ ጠገብ የሆነ ጥያቄን ለማስተናገድ ትላንት፤ ረቡዕ ግንቦት 19፤ 2012 በሩን ክፍት አድርጎ ነበር። በአዳራሹ ስብሰባ ለማካሄድ ጥሪውን ያቀረበው አካል፤ ከአራት ሰዎች በላይ በአንድ ቦታ መሰብሰብ የሚከለክለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላለመጣስ “በልዩ...

በሶማሌ ክልል ምክር ቤት ምን ተከሰተ?

6 ደቂቃ ንባብ
በሐይማኖት አሸናፊ ከ10 ወራት በኋላ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 13፤ 2012 አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሄደው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ በከፍተኛ ተቃውሞ ተስተጓጉሎ...

የሕይወት ተፈራ አዲስ መጽሐፍ ገበያ ላይ ሊውል ነው

3 ደቂቃ ንባብ
በተስፋለም ወልደየስ “ማማ በሰማይ” (Tower in the sky) በተሰኘው መጽሐፏ ይበልጥ የምትታወቀው ሕይወት ተፈራ የጻፈችው አዲስ ታሪካዊ ልብወለድ ገበያ...

ምስራቅ ኢትዮጵያ – ለኮሮና እጅ ያሰጠን ይሆን?

11 ደቂቃ ንባብ
በሐይማኖት አሸናፊ እና ተስፋለም ወልደየስ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በያዝነው ሳምንት ይፋ ካደረጋቸው የተረጋገጡ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መካከል አራቱ ከፑንትላንድ የመጡ ግለሰቦች መሆናቸውን አስታውቋል። ግለሰቦቹ በጅግጅጋ አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ እንደሆነም ተገልጿል። ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ የሌለው እና በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉባ ኮሪቻ ወረዳ...

የኮሮና ወረርሽኝ ያጠላበት የረመዳን ዋዜማ በድሬዳዋ

3 ደቂቃ ንባብ
በሐይማኖት አሸናፊ  ወትሮውንም ግርግር የማያጣት ድሬዳዋ በረመዳን ጾም መያዣም ምግብ፣ የቤት እቃ፣ ጭሳጭስ እና ሌሎች ለረመዳን ወር አስፈላጊ ነገሮችን በሚገበያዩ ነዋሪዎቿ ደምቃ ውላለች፡፡ በጾመኞች የሚዘወተሩት ሩዝ፣ አብሽ፣ ምስር፣ ቴምር፣ የተለያዩ ጁሶች፣ የስንዴ ዱቄት እና ጣፋጭ ምግቦች ዛሬ በድሬዳዋ ገበያ በሰፊው ሲገበዩ የነበሩ ናቸው፡፡ 

የጤና ሚኒስትሯ ስለ ኮሮና ወረርሽኝ ምን አሉ?

8 ደቂቃ ንባብ
በሐይማኖት አሸናፊ ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን ቁጥር አለመደበቋን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናገሩ፡፡ ነገር ግን ቁጥሩ አሁን ያለው ብቻ ነው ብሎ በእርግጠኝነት መናገር እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ሊያ ይህን የገለጹት ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገር ደረጃ እየተደረገ ባለው ዝግጅት እና እየተከናወነ...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመብት እገዳዎችን የመደንገግ ስልጣን “ገደብ የለሽ አይደለም” ተባለ

3 ደቂቃ ንባብ
በተስፋለም ወልደየስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አማካኝነት የተሰጠው የመብት እገዳዎችን የመደንገግ ስልጣን ገደቦች እንደተጣሉበት ተገለጸ። ምክር ቤቱ የሚያወጣቸው ደንቦች እና የሚወስዳቸው እርምጃዎች የመንግስት ስያሜን፣ የኢ-ሰብዓዊ አያያዝ መከ’ልከልን፣ የእኩልነት መብትን እንደዚሁም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መብቶችን “በማንኛውም ሁኔታ መገደብ አይችሉም” ተብሏል።

የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዋ ሰለባ የቀብር ስነ ስርዓት በድጋሚ ተከናወነ

5 ደቂቃ ንባብ
በተስፋለም ወልደየስ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያዋ ሰለባ የሆኑት የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት እናት የቀብር ስነ ስርዓት በድጋሚ ተከናወነ። የመጀመሪያው የቀብር ስነ ስርዓት ያለ ሟች ቤተሰብ እውቅና እንዲከናወን አድርገዋል የተባሉ አንድ የአዲስ አበባ ከተማ የየካ ክፍለ ከተማ ኃላፊም ከስራቸው መባረራቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የግብር እፎይታ እንዲያደርግ የውሳኔ ሀሳብ ቀረበለት

3 ደቂቃ ንባብ
በሐይማኖት አሸናፊ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚደርሰውን ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመቀነስ ለንግዱ ሕብረተሰብ የግብር ማቅለያ እንዲደረግ የውሳኔ ሃሳብ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ቀረበ። የውሳኔ ሀሳቡን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ነው። "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" የተመለከተችው 10 ገጾች ያሉት የውሳኔ ሃሳብ የተዘጋጀው ወረርሽኙ በተለይም በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ያሉ...

የመጪው ምርጫ ዕጣ ፈንታ በፖለቲካዊ ድርድር እንዲወሰን አብሮነት ጠየቀ

2 ደቂቃ ንባብ
በሐይማኖት አሸናፊ የሶስት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው "አብሮነት ለኢትዮጵያ አንድነት" የተሰኘው ስብስብ "መጪው ምርጫ መቼ እና እንዴት ይካሄድ?" ለሚለው ጥያቄ ብቸኛ መልሱ ፖለቲካዊ በመሆኑ ድርድር እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ "የሽግግር መንግስት ማቋቋም አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑ ግልፅ እየሆነ መጥቷል" ብሏል። 

የኮሮናን ወረርሽኝ ለመከላከል በሚቀጥለው ሳምንት ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናገሩ

2 ደቂቃ ንባብ
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚቀጥለው ሳምንት ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡ መንግስታቸው በሌላው ሀገር እንደሚታየው በኢትዮጵያ ያለውን የገበያ እንቅስቃሴ መሉ ለሙሉ እንደማይዘጋም ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህንን የገለጹት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ዛሬ ቅዳሜ ፤ መጋቢት 26 ምሽት በሰጡት መግለጫ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት በቀጣይነት የሚወስዳቸው...