ዜና

አቃቤ ህግ የታገደው የእነ ጃዋር መሐመድ ንብረት ሊመለስላቸው አይገባም አለ

በተስፋለም ወልደየስ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከጃዋር መሐመድ ቤት በብርበራ የተወሰዱ ገንዘቦች እና ዕቃዎች ፖሊስ በኢግዚቢትነት የያዛቸው ስለሆነ ልጠየቅበት አይገባም አለ። አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሶስት ተጠርጣሪዎች እና በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስም የተመዘገቡ እና በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ስድስት መኪኖችም በወንጀል ድርጊት የተገኙ ንብረቶች ስለሆኑ ሊመለሱ እንደማይገባ ተከራክሯል።   አቃቤ...

የችሎት ውሎ፦ “በሀገሪቱ ሰላም እና ደህንነት እንዲመጣ ከተፈለገ በዋስትና ወጥተን በመጪው ምርጫ መሳተፍ አለብን”- እስክንድር ነጋ

በተስፋለም ወልደየስ   የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር በሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ የሀገሪቱ ሰላም እና ደህንነት የሚፈለግ ከሆነ እርሳቸው...

ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባልታጠቁ ሲቪሎች ላይ ግድያዎች ተፈጽመዋል አለ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጸሙ ጥቃቶች፤ ባልታጠቁ ሲቪሎች ላይ ግድያዎች ተፈጽመዋል አለ። ቢያንስ በሁለት ዙር ተፈጽመዋል በተባሉ በእነዚህ...

አቶ ልደቱ አያሌው ጠበቆቻቸውን አሰናበቱ

በተስፋለም ወልደየስ   የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት የወከሏቸውን ጠበቆች አሰናበቱ። አቶ ልደቱ እርምጃውን የወሰዱት ከዚህ በኋላ በከተማው ፍርድ ቤት የህግ ክርክር ማድረግ ባለመፈለጋቸው እንደሆነ ዛሬ ረቡዕ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል። 

በአዲስ አበባ ከባድ ተሽከርካሪዎችን በተከለከለ ሰዓት በሚያንቀሳቀሱ ላይ እስከ 6 ሺህ ብር ቅጣት ተጣለ

በበለጠ ሙሉጌታ  በአዲስ አበባ ከተማ ከቀኑ 10 እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት ድረስ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ሲያንቀሳቅሱ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ከ500 እስከ ስድስት ሺህ ብር እንደሚቀጡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው የቅጣት መጠኑን ተግባራዊ ያደረገው በከተማይቱ በስራ መውጫ ሰዓታት ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ ለመቀነስ...

መንግስት አደጋዎችን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ “ያልተቀናጀ እና ደካማ ነው” ሲል ኢዜማ ተቸ

በተስፋለም ወልደየስ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ መንግስት የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለመከላከል፣ ጉዳቶችን ለመቀነስ እና ተጎጂዎችን ለመቋቋም የሚወስደው እርምጃ “ያልተቀናጀ እና ደካማ ነው” ሲል ተቸ። ፓርቲው ዛሬ ረቡዕ መስከረም 6 ባወጣው መግለጫ የመንግስት ደካማ እርምጃ “የዜጎችን ስቃይ እያረዘመው ነው” ብሏል። 

ዋስትና ተፈቅዶላቸው የነበሩት አቶ ሚሻ አደም በድጋሚ ታስረዋል ተባለ

በተስፋለም ወልደየስ   ለጃዋር መሐመድ የሳተላይት መሳሪያ በመግጠም የተከሰሱት አቶ ሚሻ አደም ዛሬ በነበራቸው ችሎት ሳይቀረቡ ቀሩ። በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዋስትና ተፈቅዶላቸው የነበሩት አቶ ሚሻ ትላንት ከእስር መፈታታቸው ቢነገርም፤ ጠበቆቻቸው ግን በኦሮሚያ ፖሊስ በድጋሚ መታሰራቸውን መስማታቸውን ዛሬ ለችሎት ገልጸዋል።  የአቶ ሚሻን...

በውጭ ሀገር የገንዘብ ምንዛሬ አገልግሎት የተጠረጠሩ ሱቆች ታሸጉ

የኢትዮጵያ መንግስት አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙትን የብር የገንዘብ አይነቶች እንዲሚቀይር በትላንትናው ዕለት ማስታወቁን ተከትሎ የ“ጥቁር ገበያ”ውን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ ተጀመረ። በአዲስ አበባ ከባንክ ውጭ የሚደረጉ የውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይቶችን በድብቅ ያከናውናሉ ከተባሉ ሱቆች መካከል የተወሰኑት ከትላንት ጀምሮ እንዲታሸጉ ተደርገዋል።  የእርምጃው ሰለባ የሆኑት በይፋ ከሚታወቁባቸው...

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነገ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ሊወያዩ ነው

በተስፋለም ወልደየስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በነገው ዕለት ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ሊወያዩ ነው። የነገው ውይይት ባለፈው ሐምሌ ወር ከተደረገው ተመሳሳይ ስብሰባ ወዲህ የነበሩ ሂደቶች የሚገመገሙበት ነው ተብሏል።  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነገ ማክሰኞ መስከረም 5፤ 2013 ረፋዱን ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው...

የእነ እስክንድር ነጋ “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ከተከሰሱ በኋላ በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት አገኘ

በተስፋለም ወልደየስ  በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ረፋዱን ክስ የተመሰረተባቸው እነ እስክንድር ነጋ፤ በስር ፍርድ ቤት አቅርበውት በነበረ አቤቱታ ከሰዓታት በኋላ ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነላቸው። እነ እስክንድር እንዲለቀቁ ውሳኔ የሰጠው ቀደም ሲል ያቀረቡትን አካልን ነጻ የማውጣት (Habeas Corpus) አቤቱታ ሲመለከት የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ...

በአዲስ አበባ በበሬ ዋጋ ላይ እስከ 10 ሺህ ብር ጭማሪ ታይቷል ተባለ

በበለጠ ሙሉጌታ በአዲስ አበባ ከተማ የቁም እንስሳት ገበያዎች በበሬ መሸጫ ዋጋ ላይ ከአምስት ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ጭማሪ መታየቱን ሸማቾች ገለጹ። በመዲናይቱ ገበያዎች አንድ በሬ ከ20 ሺህ እስከ 55 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው።    ለአዲስ ዓመት በዓል በሬ ለመግዛት በየካ...

ለጃዋር መሐመድ የሳተላይት መሳሪያ በመግጠም የተከሰሱ ባለሙያ ዋስትና ተፈቀደላቸው

በተስፋለም ወልደየስ በአቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ህገ ወጥ የሳተላይት መሳሪያ በመግጠም የተከሰሱት አቶ ሚሻ አደም ዋስትና ተፈቀደላቸው። ተከሳሹ የ20 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ዛሬ ውሳኔ የሰጠው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።  የአቶ ሚሻን ክስ እየተመለከተ የሚገኘው...

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ወቅታዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያየ

በሐይማኖት አሸናፊ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ወቅታዊ የደህንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ረቡዕ ጳጉሜ 4፤ 2012 አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ። ምክር ቤቱ ወቅታዊ የደህንነት ጉዳዮችን በዝርዝር ከተመለከተ በኋላ ስጋቶችን በተቀናጀ መልኩ መግታት የሚቻልበትን አቅጣጫ ማስቀመጡን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።  በጠቅላይ...

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የጋዜጠኞች የጉዞ ክልከላን በተመለከተ “መረጃ አልነበረኝም” አለ

በተስፋለም ወልደየስ ከነገ በስቲያ በትግራይ የሚካሄደውን ምርጫን ለመዘገብ፤ ዛሬ ወደ መቀሌ ሊጓዙ የነበሩ ጋዜጠኞች ከአውሮፕላን ጣቢያ እንዲመለሱ መደረጉን በተመለከተ ቅድሚያ መረጃ እንዳልነበረው እና ጉዳዩን እንደሚያጣራ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጸ። የጉዞ እገዳ የተደረገባቸው ጋዜጠኞች መታወቂያቸው፣ የተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው፣ ላፕቶፖቻቸው፣ ካሜራዎች እና ሌሎች የስራ ዕቃዎቻቸው...

ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእስረኛ አስተዳደር ኃላፊ በፍርድ ቤት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

በተስፋለም ወልደየስ የእነ ጃዋር መሐመድን የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ የሚመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት፤ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእስረኛ አስተዳደር ኃላፊ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው በፖሊስ ኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ላሉ ሶስት ተጠርጣሪዎች የኮሮና ምርመራ ተደርጎ፣ ውጤት እንዲቀርብ የሰጠው ተደጋጋሚ...

የኦፌኮ ምክትል ዋና ጸሀፊ በሕገ መንግስት እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ በሚፈጸም ወንጀል ተከሰሱ

በተስፋለም ወልደየስ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ በሕገ መንግስት እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ በሚፈጸም ወንጀል ተከሰሱ። አቶ ደጀኔ ክስ የቀረበባቸው ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26፤ 2012 ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው።

ኢዜማ በአዲስ አበባ የመሬት ወረራ እና የኮንዶሚኒየም ዕደላን በተመለከተ “የወንጀል ይጣራልኝ” አቤቱታ ሊያስገባ ነው

በተስፋለም ወልደየስ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት ሲከናወኑ ነበሩ ባላቸው የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ህገ ወጥ ዕደላን በተመለከተ፤ በማስረጃ የተደገፈ “የወንጀል ይጣራልኝ” አቤቱታ ለፍትህ ተቋማት ሊያስገባ እንደሆነ አስታወቀ። ከመሬት ወረራ እና ያለ አግባብ ከተከናወኑ የመሬት ዕድላዎች...

የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዶ/ር እንድርያስ ጌታን የዞኑ አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ

በተስፋለም ወልደየስ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዛሬ አርብ ነሐሴ 22 ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ፤ ባለፈው ሳምንት በብልጽግና ፓርቲ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ በተደረጉት አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ምትክ ዶ/ር እንድርያስ ጌታን የዞኑ አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ። ምክር ቤቱ የዶ/ር እንድርያስን ሹመት በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ስብሰባውን የታደሙ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር”...