ጥበብ

የሰሜን ዕዝ ጥቃት እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት እገታን የሚያስቃኝ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

በሃሚድ አወል መቀመጫውን በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ አድርጎ በነበረው የሰሜን ዕዝ የ20ኛ ክፍለ ጦር ማዘዣ ጣቢያ ላይ በጥቅምት 2013 ዓ.ም የደረሰውን ጥቃት በዝርዝር የሚያስቃኝ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው። መጽሐፉ ከክፍለ ጦሩ ማዘዣ ጣቢያ በህወሓት ኃይሎች “ታፍነው” ተወስደው የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በእገታ ያሳለፏቸውን ጊዜያት እና ገጠመኞቻቸውን ይተርካል ተብሏል።         መጽሐፉን የጻፉት፤ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃቱ ሲፈጸም በስፍራው ላይ...

የአነጋጋሪዋ ቃለ መጠይቅ አድራጊ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው

በተስፋለም ወልደየስ  በኤልቲቪ ቴሊቪዥን ጣቢያ ታቀርባቸው በነበሩ አነጋጋሪ ቃለ መጠየቆቿ የምትታወቀው ቤተልሔም ታፈሰ፤ የስራ እና የግል ህይወቷን የተመለከቱ ማስታወሻዎችን ያሰፈረችበት መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው። “እኔ...

መዓዛ መንግሥቴ ከቡከር ሽልማት የመጨረሻ ስድስት እጩዎች አንዷ ሆና ተመረጠች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊት ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ ለስመ ጥሩው የቡከር ሽልማት የመጨረሻ ዙር ከታጩ ስድስት ጸሐፍት አንዷ ሆና ተመረጠች። መዓዛ ለሽልማቱ የታጨችው “ዘ ሻዶው ኪንግ”...

የሙዚቃ አልበሞች ያላደመቁት የዘመን መለወጫ ዋዜማ

በአለምፀሀይ የኔዓለም በሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ አዲስ ዓመት ሲቃረብ የሚጠበቅ አንድ ሁነት አለ - የአዳዲስ አልበሞች ለገበያ መቅረብ። በጣት በሚቆጠሩት የጳጉሜ ቀናት ለምርጫ እስኪያስቸግር ድረስ የሙዚቃ አልበሞች ተደራርበው የሚወጡበት ነበር።   የሙዚቃ ገበያው እንደድሮው አይደለም በተባለለት ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ጊዜ እንኳ ከሐመልማል አባተ እስከ አቡሽ ዘለቀ፣ ከዘሩባቤል ሞላ እስከ ፀደንያ ብርሀኑ (ጸዲ)...

የኢህአፓው መስራች ብርሃነመስቀል ረዳ የትግል ታሪክ በመጽሐፍ ታተመ

በተስፋለም ወልደየስ ከኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) መስራቾች አንዱ የነበረው የብርሃነመስቀል ረዳ የትግል ታሪክ በባለቤቱ ታደለች ኃይለሚካኤል ተጽፎ ለንባብ በቃ። “ዳኛው ማነው?” የሚል ርዕስ የተሰጠው ይሄው መጽሐፍ የኢህአፓ ታጋይ የነበሩት የመጽሐፉ ደራሲ ታሪክንም በጥምር ያካተተ ነው።  ከጥንስሱ እስከ ህትመቱ አርባ ዓመታት ገደማ የወሰደው ይህ መጽሐፍ ታትሞ ገበያ ላይ የዋለው ከትላንት በስቲያ...

የብርጋዴየር ጄነራል ውበቱ ፀጋዬ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታትሞ ለንባብ በቃ

በተስፋለም ወልደየስበኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ውስጥ ለ32 ዓመታት ያገለገሉት ብርጋዴየር ጄነራል ውበቱ ፀጋዬ የጻፉት መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታትሞ ለንባብ በቃ። መጽሐፉ የዛሬ ሰባት ዓመት ግድም በአሜሪካ ታትሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲሰራጭ ቢቆይም ለኢትዮጵያ ገበያ ሲቀርብ የመጀመሪያው ነው።  “ሁሉም ነገር ወደ ሰሜን ጦር ግንባር” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የጄነራሉ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታትሞ መሰራጨት የጀመረው...

የሕይወት ተፈራ አዲስ መጽሐፍ ገበያ ላይ ሊውል ነው

በተስፋለም ወልደየስ “ማማ በሰማይ” (Tower in the sky) በተሰኘው መጽሐፏ ይበልጥ የምትታወቀው ሕይወት ተፈራ የጻፈችው አዲስ ታሪካዊ ልብወለድ ገበያ ላይ ሊውል ነው። መጽሐፉ በ18ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ የመሪነት ሚና በነበራቸው በእቴጌ ምንትዋብ ታሪክ ላይ ያጠነጥናል። በክፍለ ዘመኑ ለዘጠኝ ዓመታት ብቻ በንግስና የቆዩት የአጼ ባካፋ ባለቤት እቴጌ ምንትዋብ፤ ከባላቸው ሞት በኋላ በነበሩት...