ፊቸርስ

ኮምቦልቻ – የውጊያ ዳፋ እና ሥጋት የበረታባት ከተማ

ከደሴ በስተደቡብ 25 ኪሎ ሜትር ገደማ የምትርቀው የኮምቦልቻ ከተማ፤ በመጪው ረቡዕ አንድ አመት የሚሞላው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ላፈናቀላቸው በሺህዎች ለሚቆጠሩ የሰሜን እና የደቡብ ወሎ ሰዎች መጠለያ ሆናለች። ከተፈናቃዮቹ መካከል አቅማቸው የፈቀደ ቤት ተከራይተዋል፤ ወዳጅ ዘመድ ያላቸው መጠጊያ አግኝተዋል፤ ያልሆነላቸው በርከት ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ጎዳና ወድቀዋል። በጥቅምት መጀመሪያ ወደ ኮምቦልቻ ከተማ ብቅ ያለው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ሃሚድ አወል፤ በወሎ እየተካሄደ ያለው...

ትግራይ እንዴት ሰነበተች? (የመጨረሻ ክፍል)

- የአዲግራት የሁለት ሰዓታት ቆይታ- የትግራይ ተጓዦች በአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ምን ገጠማቸው?  በተስፋለም ወልደየስዕኩለ ቀን ሆኗል። ቢጫና ነጭ ቀለም የተቀቡት እና በዋናው መንገድ መሃል...

ትግራይ እንዴት ሰነበተች? (ክፍል 3)

- የውቅሮ እና ዕዳጋ ሐሙስ የወፍ በረር ቅኝት በተስፋለም ወልደየስ ድንገት ከእንቅልፌ ባነንኩ። ተከታታይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ የሰማሁ መስሎኛል። “በህልሜ ነው በእውኔ?” የሚል ጥያቄ ለራሴ አቅርቤ...

ትግራይ እንዴት ሰነበተች? – (ክፍል 2)

በተስፋለም ወልደየስ አረፋፍጄ ነው ከእንቅልፌ የተነሳሁት። ትላንት አመሻሽ ላይ በነበርኩበት የኮፊ ሃውስ በረንዳ ላይ ወደተዋወቅሁት ወጣት ደወልኩ። ካረፍኩበት ሆቴል አቅራቢያ ቁርስ ቤት አገኝ እንደሁ እንዲጠቁመኝ ነበር አደዋወሌ። ወደ መቐለ በተጓዝኩ ቁጥር ቁርስ ቤቶቻቸውን የማደን ልማድ አለኝ። የከተማይቱ ቁርስ ቤቶች የሚሰሯቸው ምግቦች ጥዑም ናቸው። ከፉል እስከ ፈታ ያሉ ምግቦች እዚህ በጣፈጠ...

ትግራይ እንዴት ሰነበተች? – (ክፍል 1)

የፈዘዘችው እና ያኮረፈችው መቐለ በተስፋለም ወልደየስ ወደ መቐለ ለመጓዝ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እየሄድኩ ነው። ወደ ከተማይቱ በየዕለቱ ይደረግ የነበረው የአውሮፕላን በረራ እንደገና ከተጀመረ ገና ሶስተኛ ቀኑ ነው። ታህሳስ 17፤ 2013። ለአምስት ሰዓት በረራ፤ በአራት ሰዓት ላይ ቀድሜ እንድገኝ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ሰራተኛ በተነገረኝ መሰረት፤ በሰዓቱ በአውሮፕላን ማረፊያው ተገኝቻለሁ።  በሞባይል አማካኝነት በኦንላይን...

ጅቡቲያዊው የጦር አውሮፕላን አብራሪ – ከኢትዮጵያ እስከ ጋቦዴ ወህኒ ቤት

ከኢትዮጵያ ተላልፎ የተሰጠው ጂቡቲያዊው የአየር ኃይል አብራሪ ፉአድ ዩሱፍ አሊ፤ ለሁለተኛ ጊዜ በረሃብ አድማ ላይ መሆኑን ጠበቃው ዛሬ  ሐሙስ ሐምሌ 16፤ 2012 ለፈረንሳይ ዓለም አቀፍ ሬድዮ (RFI) ተናግረዋል። አብራሪው ጤንነቱ ቢቃወስም ምግብ ለመመገብ አሻፈረኝ ማለቱን ገልጸዋል። በሆስፒታል የሚደረግለትን ህክምናም “ልመረዝ እችላለሁ” በሚል ስጋት አለመቀበሉንም ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።  የቀድሞው የጅቡቲ አየር...

የኳራንቲን ቆይታ በጋዜጠኛዋ አንደበት 

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው። በዚያኑ ልክ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ወደ ለይቶ ማቆያ የሚወሰዱ ግለሰቦች ቁጥርም እየጨመረ መጥቷል። እንዲህ አይነት ግለሰቦች የምርመራቸው ውጤት እስኪታወቅ ድረስ እንዲቆዩ በሚደረግበት ቦታ ቀናትን ያሳለፈችው ሐይማኖት አሸናፊ የኳራንቲን ቆይታ በቂ የስነልቦና ዝግጅት ሳይደረግ ከተገባበት “መዘዙ ብዙ ነው” ትላለች። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት...

ምስራቅ ኢትዮጵያ – ለኮሮና እጅ ያሰጠን ይሆን?

በሐይማኖት አሸናፊ እና ተስፋለም ወልደየስ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በያዝነው ሳምንት ይፋ ካደረጋቸው የተረጋገጡ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መካከል አራቱ ከፑንትላንድ የመጡ ግለሰቦች መሆናቸውን አስታውቋል። ግለሰቦቹ በጅግጅጋ አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ እንደሆነም ተገልጿል። ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ የሌለው እና በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉባ ኮሪቻ ወረዳ የሚኖር የ23 ዓመት ወጣትም እንዲሁ በኮሮና...

በኢትዮጵያ የኮሮና የመጀመሪያዋ ሰለባ የስንብት ጉዞ

በሐይማኖት አሸናፊ ከመገናኛ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ የሚጓጉዙ መንገደኞች ገብርኤል ቤተክርስቲያን መዳረሻ አካባቢ ሲደርሱ ትኩረታቸውን ቆንጥጦ የሚይዝ አንድ መደብር አለ፡፡ መደብሩ ሸቀጣ ሸቀጦችን የያዘ አይደለም፡፡ አሊያም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ ከተነገረ በኋላ ተፈላጊነታቸው እና ዋጋቸው ያሻቀበው ሳንታይዘር እና የፊት መሸፈኛም አይሸጡብትም፡፡ ይልቁንም በመደብሩ በብዛት ተደርድረው የሚታዩት የሬሳ ሳጥኖች ነው፡፡ በአካባቢው ባለው...