ላለፈው አንድ አመት ተኩል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ የነበሩት ዶ/ር ነመራ ገበየሁ ማሞ የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። ዶ/ር ነመራ ከሰኔ 1፤ 2012 ጀምሮ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው እንዲሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንደሾሟቸው ታውቋል።
አዲሱ ተሿሚ በእንግሊዝ አገር ሱሴክስ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ የተፈጥሮ ሃብቶች ላይ ጥናቶችን በማካሄድ ሶስተኛ ዲግሪአቸውን አግኝተዋል። በኢኮኖሚክስ እና በተፈጥሮ ሃብትም ሁለት የማስተርስ ዲግሪዎችን አውሮፓ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች አግኝተዋል። ዶ/ር ነመራ የመጀመሪያ ዲግሪአቸውን ያገኙት ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ ጥናት ዘርፍ ነበር።
የስራ ህይወታቸውን ከ13 ዓመት በፊት በጎንደር ዩኒቨርሰቲ በመምህርነት የጀመሩት ዶ/ር ነመራ በተማሩበት የሱሴክስ ዩነቨርሲቲ ረዳት መምህር ሆነው በማስተማርም አገልግለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሆነው እስከሚሾሙ ድረስ በእንግሊዝ አገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥም አስተምረዋል፡፡ (በሐይማኖት አሸናፊ- ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)