የመራጮች ምዝገባ ተራዘመ

ምስላዊ መረጃ፦ ዛሬ የካቲት 22 ሊጀመር ቀን ተቆርጦለት የነበረውን የመራጮች ምዝገባ፤ ወደ ቀጣዩ ወር መጋቢት አጋማሽ መዛወሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ ለቀኑ መራዘም በምክንያትነት ከጠቀሳቸው ውስጥ የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤቶችን ለመክፈት በክልል መንግስታት በኩል የታየው ዳተኝነት፣ የዕጩዎች ምዝገባ መራዘም እና የምርጫ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የገጠመው ተግዳሮት ይገኙባቸዋል። በተሻሻለው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 16 ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 15 ይካሄዳል ተብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)