ምስላዊ መረጃ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከዛሬ ቅዳሜ የካቲት 27 ጀምሮ ለመጪው አንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ዋጋ ተመን በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል። እስከ መጋቢት መጨረሻ የሚዘልቀው አዲሱ ተመን ከቀላል ጥቁር ናፍጣ በስተቀር በሁሉም የነዳጅ ምርቶች ላይ ጭማሪ አስከትሏል።
ከፍተኛ ጭማሪ የታየበት የአውሮፕላን ነዳጅ መሸጫ ሲሆን ባለፈው ከነበረበት በ3 ብር ከ53 ሳንቲም አሻቅቧል። ለምግብ ማብሰያነት አገልግሎት ላይ የሚውለው ኬሮሲን በዚህ ወር ይሸጥበት ከነበረው በ14 ሳንቲም ጨምሯል። በአንጻራዊነት በቤንዚን ላይ አነስተኛ የሚባል የ4 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጓል።
ባለፉት ሶስት ወራት የነዳጅ ዋጋ በምን ያህል መጠን እንደጨመረ ለማወቅ ከላይ የተያያዘውን ምስላዊ መረጃ ይመልከቱ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)