ምርጫ 2018
ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ምርጫ የሚጠቀምበትን ምልክት እና ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ለመጪው ምርጫ ያዘጋጀው ማኒፌስቶ በዋናነት ትኩረት ያደረገው፤ “በመግባባት፣ በመፍታት፣ በማስፋት እና በመገንባት” ላይ መሆኑን መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ። የምርጫ ማኒፌስቶዉ ዋነኛ እሳቤ “ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር መትጋት” እንደሆነም ገልጸዋል።
አቶ አደም ይህን የገለጹት፤ የሰባተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ባደረገበት መድረክ...
የአብን የፓርላማ አባሉ ዶ/ር አበባው ደሳለው በመጪው ምርጫ ኢሕአፓን ወክለው ሊወዳደሩ ነው
በሰኔ 2013 ዓ.ም በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን ወክለው የፓርላማ አባል የሆኑት ዶ/ር አበባው ደሳለው፤ በመጪው ምርጫ ኢሕአፓን ወክለው ሊወዳደሩ ነው። የአብን የአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር ይህዓለም ታምሩም በተመሳሳይ መልኩ የፓርቲ ለውጥ አድርገው በመጪው ምርጫ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዛሬ ማክሰኞ ጥር...
ለመጪው ምርጫ የሚወዳዳሩ ዕጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 16 ተራዘመ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ግንቦት መጨረሻ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩዎች ምዝገባ የሚያከናወኑበትን ጊዜ እስከ የካቲት 16፤ 2018 አራዘመ። ቦርዱ የምዝገባ ጊዜውን ያራዘመው፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቋሙ ባዘጋጃቸው የተለያዩ መድረኮች ላይ እና በጽሁፍ ጭምር ባቀረቡት ጥያቄ መሆኑን አስታውቋል።
ምርጫ ቦርድ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ይፋ ባደረገው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ፤...
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለፓርላማ አባልነት በድጋሚ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) በመወከል በባህር ዳር ከተማ ምርጫ ክልል ተመርጠው ላለፈው አራት ዓመት ተኩል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቆዩት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ በመጪው ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ። ዶ/ር ደሳለኝ ራሳቸውን ለምርጫ በዕጩነት ላለማቅረብ የወሰኑት ነጻ፣ ሰላማዊ እና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል “ምቹ መደላድል ባለመኖሩ” ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።
የፓርላማ አባሉ ይህን...
የምርጫ ቦርድ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት በሰባት ፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሞ ቀረበበት
በመጪው ሀገር አቀፍ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎችን ለመመዝገብ የተዘጋጀው የዲጂታል ስርዓት፤ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “ከፉክክር ሜዳው በማውጣት ህዝብን አማራጭ አሳጥቶ ለመግዛት የታሰበ የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚል ነቀፋ ቀረበበት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ የምርጫ ሂደቱን “ለመጉዳት” በመስሪያ ቤቱ “ሆን ተብሎ የሚደረግ ተግባር የለም” ሲል አስተባብሏል።
ዛሬ አርብ ጥር 15፤ 2018...
ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እና መራጮችን በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ ሊጀምር ነው
በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎች እና መራጮች በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ የሚችሉበት መተግበሪያ እና የድረ ገጽ አማራጭ ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የዲጂታል አማራጮቹ፤ በስድስት የሀገሪቱ ቋንቋዎች ምዝገባ ለማከናወን እንዲችሉ ተደርገው መዘጋጀታቸውም ተገልጿል።
ምርጫ ቦርድ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 27፤ 2018 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ የዲጂታል...
በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ያገኘ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር፤ ለቀጣዩ ምርጫ 1,200 ገደማ ዕጩዎችን ማዘጋጀቱን አስታወቀ
“ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት” የተባለው የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ፤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅንጅት ምዝገባ ምስክር ወረቀት አገኘ። የቅንጅቱ አካላት የሆኑ አራት ፓርቲዎች፤ በመጪው ምርጫው የሚወዳደሩ 1,200 ገደማ ዕጩዎችን አስቀድመው ማዘጋጀታቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
“ለኢትዮጵያ” በሚለው አጭር ቃል የሚጠራው ይኸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅንጅት፤ መመስረቱ ይፋ የተደረገው ባለፈው መስከረም ወር ነበር።...
ኢዜማ በትምህርት ሚኒስቴር ባገኘሁት ኃላፊነት “ለምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቅሙኝን ሥራዎች ሠርቻለሁ” አለ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፤ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ለምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቅመውን ሥራ መሥራቱን አስታውቀ። የፓርቲው መሪ የትምህርት ሚኒስቴርን ለመምራት ባገኙት ዕድል፤ የፓርቲውን የትምህርት ፖሊሲ “ማስፈጸማቸውን” ገልጿል፡፡
ፓርቲው ይህን ያለው፤ ሰባተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ ዛሬ ታኅሣሥ 7፤ 2018 ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው። ኢዜማ በዚሁ መግለጫው፤ በዝምታ ውስጥ ያለው ሰፊው...
የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወነው ከጥር 1 ጀምሮ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ መሆኑን ምርጫ ቦርድ...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ሆኖ መጽደቁን አስታወቀ። ቦርዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ባደረገው የጸደቀ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ፤ የምርጫ ውጤት በቦርዱ ደረጃ ይፋ የሚደረገው ሰኔ 4 ቀን እንደሆነ ገልጿል።ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 30፤ 2018 ይፋ የተደረገው የጊዜ ሰሌዳ፤ በረቂቅ ደረጃ ከነበረው...
የኢትዮጵያ መንግስት በምርጫ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ “አፋጣኝ” እና “ተጨባጭ” እርምጃዎችን እንዲወስድ ዘጠኝ ተቃዋሚ የፖለቲካ...
ስለመጪው ምርጫ ሂደትም ሆነ የጊዜ ሰሌዳን የተመለከተ ውይይት ከመደረጉ አስቀድሞ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰባት መሰረታዊ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ “አፋጣኝ” እና “ተጨባጭ” እርምጃዎችን እንዲወስድ ዘጠኝ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የፓርቲዎች ስብስብ ጠየቁ። መንግስት እና ገዢው ፓርቲ ቅድመ ሁኔታዎቹን በማሟላት፤ ለሁሉም ወገኖች “ነጻ እና ፍትሃዊ የሆነ” የውድድር ምህዳር እንዲፈጥሩ ፓርቲዎቹ ጥሪ...
በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ያሉ የጸጥታ ሁኔታዎችን መከታተል የሚያስችል “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት” ሊዘረጋ መሆኑን ምርጫ...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ያሉ የጸጥታ ሁኔታዎችን የሚከታተልበት “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት” (early warning system) ለመዘርጋት ጥናት እያደረገ መሆኑን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አስታወቁ። ቦርዱ ባለፈው ሳምንት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባካሄደው ስብሰባ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ስጋቶች መንጸባረቃቸውን የገለጹት ዋና ሰብሳቢዋ፤ ሆኖም “ምርጫው ይራዘማል የሚል ነገር...
ምርጫ ቦርድ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በግንቦት 24 ለማካሄድ ምክረ ሃሳብ አቀረበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24፤ 2018 ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቀረበ። ቦርዱ በምርጫው የሚገኘውን ውጤት ይፋ ለማድረግ፤ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ያስቀመጠው ዕለት ሰኔ 3፤ 2018 ነው።
ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫውን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ለውይይት ያቀረበው፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጥቅምት 10፤ 2018...
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገራዊ ምርጫ ዘንድሮ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጡ
የኢትዮጵያ መንግስት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጠ። የመንግስትን ማረጋገጫ ዛሬ ሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ላይ በይፋ ያሳወቁት፤ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ናቸው።
ታዬ በህዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የስራ ዘመን መክፈቻ ላይ ባደረጉት በዚሁ ንግግር፤ የፌደራል መንግስትን ዓመታዊ እቅድ አቅርበዋል። የፕሬዝዳንቱ ንግግር አርባ...
መጪውን ሀገራዊ ምርጫ “ፈቃጅ” እና “አስቻይ” ሁኔታዎች ባሉባቸው አካባቢዎች ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ምርጫ...
በቤርሳቤህ ገብረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ መጪው ሀገራዊ ምርጫ “ፈቃጅ” እና “አስቻይ” ሁኔታዎች ባሉባቸው የምርጫ ክልሎች እንደሚደረግ ገለጸ። በሀገሪቱ ያለው የጸጥታ ሁኔታ “በጣም ተለዋዋጭ በመሆኑ”፤ ምርጫው በሚቃረብበት ወቅት ሁኔታው “በዝርዝር” እና “በጥልቀት” የሚታይ መሆኑንም አስታውቋል።
ቦርዱ ይህንን ያስታወቀው፤ የሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 25፤...











































