ዜና
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ሁሉም ሀገራት “ድንበር ተሻጋሪ ወረራዎችን ማስወገድ ይገባቸዋል”...
ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር “በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ስለበረታው ውጥረት” በዛሬው ዕለት በስልክ የተነጋገሩት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፤ “በሁሉም ወገኖች በኩል ውጥረት ማርገብን እደግፋለሁ” አሉ። በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ሁሉም ሀገራት፤ “ድንበር ተሻጋሪ ወረራዎችን ማስወገድ ይገባቸዋል” ሲሉም አሳስበዋል።
ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ያደረጉትን ውይይት በማስመልከት አጠር ያለ...
የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ፤ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለህብረቱ ሀገራት ተወካዮች ማብራሪያ...
የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አኔት ዌበር፤ በአዲስ አበባ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በተገናኙ ማግስት፤ በኢትዮጵያ እና በአጠቃላይ በቀጠናው ሁኔታ ላይ ለህብረቱ አባል ሀገራት ማብራሪያ አቀረቡ። ዲፕሎማቷ ማብራሪያውን የህብረቱ ምክር ቤት መቀመጫ በሆነችው ብራስልስ የሰጡት፤ “በቀጥታ ከአውሮፕላን እንደ ወረዱ" እንደሆነ ገልጸዋል።
ማብራሪያቸውን ያደመጠው የህብረቱ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚቴ፤ የአውሮፓ...
በጋምቤላ ከተማ ከምሽት እስከ ንጋት የሚዘልቅ የሰዓት እላፊ ተጣለ
በጋምቤላ ከተማ ከዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 4፤ 2019 ጀምሮ ከምሽት 12 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ “ላልተወሰነ ጊዜ” የሚቆይ የሰዓት እላፊ ተጣለ። “ለጸጥታ ስራ” ሲባል እንደተጣለ በተገለጸው በዚሁ የሰዓት ገደብ ውስጥ በከተማይቱ የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ “በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን” የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን ይህን እርምጃ የወሰደው፤...
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በክልል የተሾሙ ባለስልጣናትን በድጋሚ ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሾሙ
ከአንድ ሳምንት በፊት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንን በኃላፊነት እንዲመሩ የተሾሙት አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፤ በፌደራል መስሪያ ቤት የሚኒስትር ዴኤታነት አዲስ ሹመት ተሰጣቸው። ከሁለት ሳምንት በፊት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዲሆኑ የተሾሙት ዶ/ር ቶላ በሪሶ፤ ባለፈው ቅዳሜ በተመሳሳይ መልኩ የሚኒስትር ዴኤታ ሹመት አግኝተዋል።
ለሁለቱም አመራሮች የሚኒስትር ዴኤታነት ሹመት...
የተመድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ ላይ በዝግ ሊመክር ነው
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 3፤ 2019 በወቅታዊ “የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ ላይ” በዝግ ሊመክር ነው። የዝግ ስብሰባው የተጠራው፤ “በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ መባባሱን” ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ተገልጿል።
የነገው ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቀችው በጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣን ያላት ዩናይትድ ስቴትስ እንደሆነች...
በትግራይ ክልላዊ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ፤ የፌደራል መንግስት “ሙሉ ትግራይን እንደሚያስተዳድር” አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ...
በትግራይ ክልል “ለምርጫ የሚሆን አመቺ ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ” የፌደራል መንግስት “ሙሉ ትግራይን እንደሚያስተዳድር” የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። በክልሉ በፌደራል የሚመራ “ኮማንድ ፖስት” እንደሚቋቋም የገለጹት አቶ ጌታቸው፤ በሁሉም ቦታዎች በሚካሄድ ምርጫ የወረዳ አስተዳዳሪዎች እንደሚሰየሙ አስታውቀዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪነታቸው እንዲቀጥሉ በትላንትናው...
የቀድሞዋ መከላከያ ሚኒስትር፤ የአፋር ክልል የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን በኃላፊነት እንዲመሩ ተሾሙ
በትላንትናው ዕለት በተመሰረተው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ካቢኔ ውስጥ ሳይካተቱ የቀሩት የቀድሞዋ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ፤ በአፋር ክልል መንግስት ሹመት ተሰጣቸው። የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አይሻ፤ የአፋር ክልል የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን በኃላፊነት እንዲመሩ በዛሬው ዕለት መሾማቸውን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
አራት የፌደራል መስሪያ ቤቶችን በሚኒስትርነት የመሩት አይሻ፤ ወደ ተወለዱበት...
በትግራይ እና አዋሳኝ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን ሁኔታ “የትጥቅ ግጭት” አድርጎ እንደሚወስደው ኢሰመኮ ገለጸ
በትግራይ ክልል እና በአዋሳኝ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለውን ውጊያ፤ ብሔራዊው የሰብአዊ መብት ተቋም የሚጠራው “ጦርነት” በሚለው ስያሜ ሳይሆን “የትጥቅ ግጭት” በሚለው ብየና እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ተናገሩ። የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን በተመለከተ ኮሚሽኑ “መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ” መሆኑንም አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።
የኢሰመኮ ዋና...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከነገ በስቲያ ዳግም ሊጀምር ነው...
ላለፉት ሶስት ሳምንታት ተቋርጦ የቆየው በአዲስ አበባ እና በመቐለ ከተሞች መካከል የሚደረገው የአውሮፕላን መደበኛ በረራ፤ ከነገ በስቲያ እሁድ ጥቅምት 1፤ 2019 ጀምሮ በድጋሚ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ ደንበኞቹ የጉዞ ምዝገባቸውን ከዛሬ ጀምሮ ማካሄድ እንደሚችሉ ገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርጋቸውን በረራዎች “በጊዜያዊነት” ያቋረጠው ከመስከረም 13፤...
11 አዲስ፣ 9 በነበሩት የቀጠሉ እና 3 ወደ ሌላ መስሪያ ቤት የተዛወሩ ሚኒስትሮችን የያዘው...
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ መስከረም 28፤ 2019 ባካሄደው ስብሰባ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን 23 የካቢኔ አባላት ሹመት አጽድቋል። ባለፈው ሰኞ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመቀጠል ቃለ መሃላ የፈጸሙት አብይ ዛሬ ስራ አስፈጻሚውን ሲያዋቅሩ፤ ከቀደመው መንግስታቸው የካቢኔ አባላት መካከል 9 ሹማምንት በስልጣናቸው ቀጥለዋል።
ሶስቱ ሚኒስትሮች ወደ ሌሎች መስሪያ...
በትግራይ ክልል የሚገኙ የሰብአዊ እርዳታ መጋዘኖች መዘረፋቸውን የመንግስታቱ ድርጅት አስታወቀ
በትግራይ ክልል በሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) መጋዝን ላይ ከትላንት በስቲያ እሁድ ዘረፋ መፈጸሙን የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ ምክትል ቃል አቃባይ ገለጹ። በክልሉ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ የዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ድርጅቶች መጋዘኖች እና መገልገያዎች በተመሳሳይ መልኩ መዘረፋቸውንም ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ምክትል ቃል አቃባይ ፋራህን...
“የውጭ ግንኙነታችን የኢትዮጵያን ተጽዕኖ በአለም ላይ ሊያሳይ በሚችል መልኩ እንዲቃኝ ይደረጋል” – ጠቅላይ ሚኒስትር...
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት የሀገሪቱን “ተጽዕኖ በዓለም ላይ ሊያሳይ በሚችል መልኩ” እንዲቃኝ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። “ፍላጎታችን ኢትዮጵያ በዓለም እንድትለወጥ ሳይሆን፤ ራሷም ገዝፋ ዓለምን እንድትለውጥ ማድረግ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።
አብይ ይህን ያሉት ዛሬ ሰኞ መስከረም 25፤ 2019፤ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ላስቀጠለላቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሰሙት...
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በስልጣናቸው ላይ እንዲቀጥሉ የፓርላማ ይሁንታ አገኙ
ከመጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲመሩ የቆዩት አብይ አህመድ፤ በስልጣናቸው ላይ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት እንዲቆዩ በፓርላማ ይሁንታ አገኙ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዛሬ ሰኞ መስከረም 25፤ 2019 በተካሄደው የፓርላማ ስብሰባ ሹመታቸው በጭብጨባ ጸድቆላቸዋል።
በኢፌዲሪ ህገ መንግስት መሰረት የፌደራል መንግስትን ስልጣን የሚረከበው፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው የፖለቲካ...
ሙፈሪያት ካሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ
ከዚህ ቀደም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን በአፈ ጉባኤነት የመሩት ሙፈሪያት ካሚል፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ። ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነታቸው ባለፈው ሳምንት የተነሱት አቶ ደስታ ሌዳሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነዋል።
ሙፈሪያት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤው ሆነው ከመመረጣቸው አስቀድሞ፤ ላለፉት አምስት ዓመታት የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሆነው በመስራት...
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፤ የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ
ላለፉት ስምንት ዓመታት የገንዘብ ሚኒስቴር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት አቶ አህመድ ሽዴ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስተኛው አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ። አቶ አህመድን በአፈ ጉባኤነት የመረጡት፤ ዛሬ ሰኞ መስከረም 25፤ 2019 የሰባተኛ የምርጫ ዘመን የመጀመሪያ ስብሰባቸውን ያካሄዱት አዲስ ተመራጭ የፓርላማ አባላት ናቸው።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫዎች ውስጥ በሰባተኛው...














































