ዜና

የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶስት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነው። ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዛምቢያ የሚያደርጉት ጉብኝት፤ አሜሪካ ከየሀገራቱ ጋር ያላትን “ቁልፍ” የሁለትዮሽ ግንኙነቶች የማጠናከር እንዲሁም የጸጥታ እና የኢኮኖሚ አጋርነቶችን የማሳደግ ዓላማ ያለው ነው ተብሏል። ጋርሺያ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ረዳት ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በነገው ዕለት...

ኢዜማ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ምክረ ሃሳቦችን የሚከታተል “ገለልተኛ እና ህጋዊ” አካል አንዲቋቋም ጠየቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን አተገባበር የሚከታተል “ገለልተኛ እና ሕጋዊ” አካል አንዲቋቋም ጥያቄ አቀረበ። የፌደራል...

ከዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች መካከል 87.2 በመቶው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያሳልፍ ውጤት ማምጣት አልቻሉም 

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት “በአብዛኛው ደስተኞች ነን” ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከተፈታኝ ተማሪዎች...

በአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ አቀራራቢ ሃሳቦችን እንዲያዘጋጅ የተቋቋመው ኮሚቴ፤ አስማሚ ምክረ ሃሳቦችን ዛሬ ያቀርባል...

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ውዝግብ እና አለመግባባት በፈጠረው የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ላይ አስማሚ ሃሳብ እንዲያዘጋጅ የተቋቋመው አቀራራቢ ኮሚቴ፤ የደረሰበትን ውጤት በዛሬው ዕለት ለተመካካሪዎች እንዲያቀርብ መወሰኑን የጉባኤው ተሳታፊዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። ኮሚቴው አስማሚ ሃሳቡን የሚያዘጋጀው፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ደረጃዎች የተከፋፈሉ ቡድኖች ያቀረቧቸውን ሃሳቦች ከቃለ ጉባኤዎች ላይ ከመረመረ...

በመጠናቀቅ ላይ ባለው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ 476 ምክረ ሃሳቦች መቅረባቸው ተገለጸ  

በቀጣዮቹ ቀናት ይጠናቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ፤ በስምንት ዋነኛ መወያያ አጀንዳዎች ስር በአጠቃላይ 476 ምክረ ሃሳቦች መቅረባቸው ይፋ ተደረገ። የቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ከተጠቃለሉ እና ከተጣጠሙ በኋላ የተዘጋጀውን አንድ ወጥ ሰነድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነገ አርብ አሊያም ከነገ ወዲያ ቅዳሜ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል። በ90 ንዑሳን አጀንዳዎች እና በ225...

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ “የጽምጽ ውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት” ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑን ተሳታፊዎች ገለጹ 

ሰላሳ አራተኛ ቀኑን በያዘው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ በአጀንዳዎች ላይ ውሳኔ እየተሰጠ ያለው “የድምጽ አሰጣጥ ስርዓትን” በተከተለ አግባብ አለመሆኑን ሶስት የጉባኤው ተሳታፊዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በጉባኤው ላይ በማመካከር እና በታዛቢነት እየተሳተፉ ያሉ ሁለት ግለሰቦችም ይህንኑ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው ሰነድ በአጀንዳዎች ላይ ውሳኔ የሚደረሰው በየደረጃው ያሉ ተሳታፊዎች...

በእስር ላይ የሚገኙት የኢሕአፓ አባላት እና የፓርቲው ጠበቃ፤ የ12 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደባቸው

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ባለፈው ሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አባላት አቶ አበበ አካሉ እና አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እንዲሁም የፓርቲው ጠበቃ አቶ አበራ ንጉስ ላይ ፍርድ ቤት የ12 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ፣ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ...

የ“አዲስ ስታንዳርድ” ዋና አዘጋጅ ታስሮ መለቀቁን እና የድርጅቱ ንብረቶች በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸውን አሳታሚው አስታወቀ

የ“አዲስ ስታንዳርድ” የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከድር፤ ባለፈው ቅዳሜ “በጸጥታ አባላት” ተይዞ ከአንድ ቀን በኋላ መለቀቁን አሳታሚ ድርጅቱ አስታወቀ። ይህ ድርጊት በተፈጸመ በማግስቱ “የጸጥታ እና የደህንነት አባላት” ወደ “አዲስ ስታንዳርድ” ቢሮ በመግባት፤ መገናኛ ብዙሃኑ ለስራ የሚገለገልባቸውን ንብረቶች ይዘው መሄዳቸውንም ድርጅቱ ገልጿል። የመገናኛ ብዙሃኑ አሳታሚ ጃኬን ፐብሊሺንግ ኃላፊነቱ...

ፖሊስ ሁለት የኢህአፓ አባላትን እና የፓርቲውን ጠበቃ “የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ወነጀለ   

ከትላንት በስቲያ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሁለት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አባላት እና የፓርቲው ጠበቃ፤ “የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል” የሚል ውንጀላ ቀረበባቸው። ፖለቲከኞቹ እና ጠበቃው ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት (ህወሓት)፣ “ከሌሎች ጸረ- ሰላም ኃይሎች” እና “ጽምዶ” ተብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር “በመቀናጀት” በአዲስ አበባ ከተማ አባላትን “በመመልመል” እና “በማደራጀት” ተጠርጥረዋል።  የፌደራል...

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ከተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በላይ ሊወስድ ይችላል ተባለ

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፤ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየሄደ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጸ። እስካሁን በጉባኤው የተጠናቀሩ አጀንዳዎች፤ ከሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ 500 ተመካካሪዎችን ለሚይዙ 8 ቡድኖች እንደሚቀርቡ ኮሚሽኑ አስታውቋል።  ከሁለት ሳምንት በፊት ሐምሌ 8፤ 2018 በይፋ የተከፈተው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፤...

የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ በኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ልሂቃን እና በሌሎች ተመካካሪዎች መካከል አለመግባባት ፈጠረ

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ትኩረት ከሳቡ አጀንዳዎች አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ፤ በኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ልሂቃን እና በሌሎች ተመካካሪዎች መካከል አለመግባባት ፈጥሯል። “አዲስ አበባ የፌደራል ትሁን ወይስ የኦሮሚያ ክልል አካል?” የሚለው ጥያቄ በጉባኤው ከተደራጁ ጥቃቅን ቡድኖች እስከ ስልታዊ ቡድኖች ድረስ ተንጸባርቋል። ትላንት ረቡዕ ሐምሌ...

የህገ መንግስቱ አንቀጽ 39 ጉዳይ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ እያከራከረ ነው

በይፋ ከተከፈተ አንድ ሳምንት ባስቆጠረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ተወካዮች፤ በስምንት ዋነኛ አጀንዳዎች በተከፋፈሉ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ይገኛሉ። ከእነዚህ ዋነኛ አጀንዳዎች መካከል “የመንግስት አደረጃጀት እና ቅርጽ” እንዲሁም “የፖለቲካ ስርዓት፣ የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርዓትን” የሚመለከተው ይገኝበታል። በዚህ አጀንዳ ስር በንዑስ አጀንዳነት ከተያዙ የውይይት ጉዳዮች ውስጥ፤ “የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና...

ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት 215 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ33.2 በመቶ ዕድገት ያሳየ ነው። መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ለተመዘገበው ዕድገት እንደ አንድ ምክንያት የጠቀሰው የገቢ ምንጮቹ መስፋፋትን ነው። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 16፤ 2018...

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ “ጠንካራ ተቃውሞ” የሚያጋጥማቸው አጀንዳዎች፤ ወደ ህዝበ ውሳኔ ሊመሩ እንደሚችሉ ተገለጸ

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ውሳኔ ላይ የሚደረስባቸው፤ በየደረጃው ያሉ ተሳታፊዎች ከ70 እስከ 75 በመቶ ድጋፍ ሲያገኝ እንደሆነ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተዘጋጀ ሰነድ አመለከተ። ሁሉንም የውሳኔ ሂደቶች አልፈው ለጠቅላላ ጉባኤ ከቀረቡ በኋላ “ጠንካራ ተቃውሞ” የሚያጋጥማቸው አጀንዳዎች፤ ወደ ህዝበ ውሳኔ “ሊመሩ” እንደሚችሉበሰነዱ ላይ ተጠቁሟል። በ30 ገጾች የተዘጋጀው ይህ ሰነድ...

“ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሽ ሲል የሚነቁ፤ የጠላትነት ስሜት ያላቸው ሀገራት አሉ” – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ...

“ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሽ ሲል፤ ያደፈጡ፣ የሚነቁ፣ የዘመናት ያልተቋረጠ የጠላትነት ስሜት ያላቸው ሀገራት አሉ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ኢትዮጵያ “በቀጣይ” አዲስ ህገ መንግስት ሊኖራት እንደሚችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቆማ ሰጥተዋል። አብይ ይህን ፍንጭ የሰጡት ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 8፤ 2018 ዓ.ም. በይፋ በተከፈተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።...

“ሁሉም የዲጂታል ሚዲያዎች” ምዝገባ እንዲያከናውኑ ለማድረግ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ ሊደረግ ነው

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ “ሁሉም የዲጂታል ሚዲያዎች” ወደ ምዝገባ ስርዓት እንዲገቡ ለማስቻል፤ በስራ ላይ ያለውን የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ እስከ ማሻሻል የሚደርስ “የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን” እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ። መስሪያ ቤቱ “በበየነ መረብ የሚያጋጥሙ” ባላቸው “የስነምግባር እና የህግ ጥሰቶች” ላይ “አስተዳደራዊ እርምጃ” እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።  ባለስልጣኑ ይህን ያስታወቀው ትላንት ቅዳሜ ሐምሌ...

በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ሆቴሎች በመኝታ አገልግሎቶቻቸው ላይ አምስት በመቶ ተጨማሪ ታክስ ተጣለባቸው  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ፤ የሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከሚሰጡት የመኝታ አገልግሎት ላይ አምስት በመቶ ታክስ እንዲሰበስቡ ግዴታ የሚጥል ደንብ ተግባራዊ አደረገ። ደንቡ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ሐምሌ 1፤ 2018 ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር ቢሮው ቢገልጽም፤ የሆቴል ባለቤቶች ግን ለመዘጋጃ የተሰጠው ጊዜ አጭር መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን አስምተዋል።...

“ህገ ወጥ የሲቪል ሰዎች ግድያ”፣ “ማሰቃየት” እና “ኢ-ሰብአዊ አያያዝ” በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የሰብአዊ መብቶች...

“ህገ ወጥ የሲቪል ሰዎች ግድያ”፣ “የዘፈቀደ እና የተራዘመ እስር”፣ “አስገድዶ መሰወር እና ጠለፋ” እንዲሁም “ማሰቃየት እና ኢ-ሰብአዊ አያያዝ”፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለሰብአዊ መብቶች ትግበራ “ዋና ዋና ስጋቶች” እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተነበየ። ኮሚሽኑ በነጻ ሚዲያ እና በጋዜጠኞች ላይ “እየጨመረ መጥቷል” ያለውን “ገደብ” እና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ...