የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ “ጠንካራ ተቃውሞ” የሚያጋጥማቸው አጀንዳዎች፤ ወደ ህዝበ ውሳኔ ሊመሩ እንደሚችሉ ተገለጸ
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ውሳኔ ላይ የሚደረስባቸው፤ በየደረጃው ያሉ ተሳታፊዎች ከ70 እስከ 75 በመቶ ድጋፍ ሲያገኝ እንደሆነ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተዘጋጀ ሰነድ አመለከተ። ሁሉንም የውሳኔ ሂደቶች አልፈው ለጠቅላላ ጉባኤ ከቀረቡ በኋላ “ጠንካራ ተቃውሞ” የሚያጋጥማቸው አጀንዳዎች፤ ወደ ህዝበ ውሳኔ ”ሊመሩ” እንደሚችሉበሰነዱ ላይ ተጠቁሟል።
በ30 ገጾች የተዘጋጀው ይህ ሰነድ...
“ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሽ ሲል የሚነቁ፤ የጠላትነት ስሜት ያላቸው ሀገራት አሉ” – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ...
“ኢትዮጵያ ውስጥ ኮሽ ሲል፤ ያደፈጡ፣ የሚነቁ፣ የዘመናት ያልተቋረጠ የጠላትነት ስሜት ያላቸው ሀገራት አሉ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ኢትዮጵያ “በቀጣይ” አዲስ ህገ መንግስት ሊኖራት እንደሚችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቆማ ሰጥተዋል።
አብይ ይህን ፍንጭ የሰጡት ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 8፤ 2018 ዓ.ም. በይፋ በተከፈተው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።...
የህገ መንግስት ማሻሻያ እና የመንግስት አደረጃጀት ጉዳይ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ በአጀንዳነት መያዛቸው ተገለጸ
ከመጪው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ለሶስት ሳምንት በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ ከሚቀርቡ አጀንዳዎች መካከል የህገ መንግስት ማሻሻያ እንዲሁም የመንግስት አደረጃጀት እና ቅርጽ እንደሚገኙበት ይፋ ተደረገ። የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ጉዳይ እንዲሁም የምርጫ ስርዓት በሀገር አቀፍ ጉባኤው ለምክክር ከሚቀርቡት አጀንዳዎች ውስጥ ተካትተዋል።
የምክክር አጀንዳዎቹን ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 17፤...
በኢትዮጵያ ባሉ ግጭቶች ምክንያት ነጋዴዎች “ለግድያ”፣ “ለስደት” እና “ለንብረት ውድመት” መጋለጣቸው ተገለጸ
በኢትዮጵያ በሚከሰቱ በግጭቶች ምክንያት ነጋዴዎች “ለግድያ”፣ “ለስደት” እና “ለንብረት ውድመት” መጋለጣቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቦጋለ ቢታኔ ተናገሩ። በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ሳቢያ በክልሉ የሚገኙ ነጋዴዎች ከባንኮች ተበድረው ያልመለሱት የገንዘብ መጠን ወደ 90 ቢሊዮን ብር ማሻቀቡም ተገልጿል።
ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ንግድ እና...
ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ጀምሮ ሊካሄድ ነው
ላለፉት አራት ዓመታት ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ፤ ከአንድ ወር በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። ከሐምሌ 8፤ 2018 በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ለሶስት ሳምንታት በሚካሄደው በዚሁ ጉባኤ ላይ አራት ሺህ ሰዎች እንደሚሳተፉ ኮሚሽኑ ገልጿል።
ኮሚሽኑ ይህን የገለጸው፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚጀመርበትን ቀን አስመልክቶ ዛሬ...
የትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
ከትግራይ ክልል ለሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎች የሚሰበሰቡበት መርሃ ግብር በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። በመርሃ ግብሩ የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ ላይ 400 ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኮሚሽኑ ገልጿል።
ከተሳታፊዎቹ ውስጥ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እንደሚገኙበት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር...
በትግራይ ክልል ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የሚመክር ስብሰባ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልል የምክክር ሂደትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ለሚኖሩ እና ከክልሉ ለሚመጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች “ከፍተኛ ጥሪ” በማድረግ የምክረ-ሐሳብ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ለማከናወን ማቀዱን አስታወቀ። መርሃ ግብሩን በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ለማካሄድ መታቀዱን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በታህሳስ 2014 ዓ.ም በአዋጅ የተቋቋመው፤...
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለተጨማሪ ስምንት ወራት ተራዘመ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን በስምንት ወር አራዘመ። ፓርላማው የኮሚሽኑን የስራ ዘመን ለሁለተኛ ጊዜ ያራዘመው፤ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 11፤ 2018 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።
በታህሳስ 2014 ዓ.ም በወጣ አዋጅ የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ፤ መጀመሪያ የተሰጠው የሶስት ዓመት የስራ ዘመን ነበር። ኮሚሽኑ በተሰጠው ጊዜ ስራውን ማገባደድ...
የትግራይ አጀንዳ ማሳባሰቢያን በአዲስ አበባ ማካሄድ በአማራጭነት መያዙን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ
ለሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ የትግራይ ክልል አጀንዳዎች የሚሰባሰቡበትን መድረክ፤ በአዲስ አበባ ማካሄድ በአማራጭነት መያዙን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተራዘመለት የስራ ዘመን ሊጠናቀቅ በመቃረቡ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የምክክር ጉባኤ “በፍጥነት” እንዲጀምር ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል።
ማሳሰቢያውን የሰጠው፤ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ትላንት አርብ...
“የታሰሩ ፋኖዎች ከእስር እንዲለቀቁ እየጠበቅን ነው”- መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ
መንግስት የታሰሩ ፋኖዎች ከእስር እንዲፈቱ “በገባው ስምምነት” መሰረት ትግበራውን እየጠበቁ መሆናቸውን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) አመራር የነበሩት መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ገለጹ። በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው በቅርቡ “ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል” መግባታቸውን የተናገሩት የአፋህድ አመራሮች፤ 17 አጀንዳዎችን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቅረባቸውን አስታውቀዋል።
የአፋህድ አመራሮች አጀንዳዎቹን ለሀገራዊ ምክክር...
ከ1,700 በላይ “የጥቃቅን ቡድኖች” የምክክር አጀንዳዎችን መሰነዱን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ
በተስፋለም ወልደየስ
እስከ ዛሬ ድረስ ባለው ሀገራዊ የምክክር ሂደት፤ ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ መሳተፋቸውን ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች አንዱ የሆኑት ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ ተናገሩ። ኮሚሽኑ ከ1,746 በላይ የሆኑ “የጥቃቅን ቡድኖች” የምክክር አጀንዳዎችን መሰነዱንም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።
ዶ/ር አምባዬ ይህን ያስታወቁት፤ ዛሬ አርብ ግንቦት 22፤ 2017 በአዲስ አበባው ሚሊኒየም አዳራሽ በተጀመረው የፌደራል...
በፌደራል ደረጃ ካሉ የባለድርሻ አካላት ሀገራዊ የምክክር አጀንዳዎችን የማሰባሰቢያ መድረክ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሊካሄድ...
በቤርሳቤህ ገብረ
በፌደራል ደረጃ ባሉ የባለድርሻ አካላት የሚደረገው የሀገራዊ ምክክር እና የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በዚህ መድረክ ላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማህበራት ተወካዮችን ጨምሮ 38 የባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ ተብሏል።
ባለፈው...
በሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚታየው የምሁራን ተሳትፎ ከሚጠበቀው አንጻር “አነስተኛ ነው” ተባለ
በቤርሳቤህ ገብረ
በኢትዮጵያ ያሉ ምሁራን በሀገራዊ የምክክር ሂደት ላይ ያላቸው ተሳትፎ፤ ሊኖራቸው ከሚገባው “አስተዋጽኦ” አንጻር ሲታይ “አነስተኛ ነው” ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ተናገሩ። አብዛኞቹ ምሁራን ከሂደቱ “ራሳቸውን የማግለል” አሊያም ሁኔታውን “በዝምታ የመመልከት” አካሄዶችን የመከተል “አዝማሚያዎች” እንደሚታይባቸውም ገልጸዋል።
ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ይህን የገለጹት፤ በሀገራዊ የምክክር ሂደት ምሁራን...
በትጥቅ ትግል እና በእስር ላይ ያሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን በምክክር ሂደት ለማሳተፍ የጀመረውን ጥረት...
በተስፋለም ወልደየስ
በተለያዩ ምክንያቶች ጫካ ገብተው ትጥቅ ትግል እያካሄዱ የሚገኙ፣ እስር ቤት ያሉ እንዲሁም ሀገራቸውን ለቅቀው የተሰደዱ የአማራ ክልል ተወላጆች፤ በሀገራዊ ምክክር እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ለመፍጠር የጀመረውን ጥረት “አጠናክሮ እንደሚቀጥል” የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ጥረቱን ከግብ ለማድረግ “የተለየ ትኩረትም ሰጥቶ” እንደሚሰራ ገልጿል።
ይህ የተገለጸው ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 2፤...
የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ሲያካሄዱት የቆየው የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተጠናቀቀ
የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ካለፈው እሁድ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲያካሄዱት የቆየው የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተጠናቀቀ። የማህበረሰብ ተወካዮቹ፤ በመጪዎቹ ቀናት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ የምክክር ሂደት የሚሳተፉ 270 ወኪሎቻቸውንም መርጠዋል።
በቁጥር ከ4,500 በላይ የሚሆኑት እነዚህ የማህበረሰብ ተወካዮች፤ በክልሉ ካሉ 263 ወረዳዎች የተመረጡ ናቸው። አስር የማህበረሰብ ክፍሎችን የወከሉት...










































