ሰሞነኛ ጉዳዮች
“ህገ ወጥ የሲቪል ሰዎች ግድያ”፣ “ማሰቃየት” እና “ኢ-ሰብአዊ አያያዝ” በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የሰብአዊ መብቶች...
“ህገ ወጥ የሲቪል ሰዎች ግድያ”፣ “የዘፈቀደ እና የተራዘመ እስር”፣ “አስገድዶ መሰወር እና ጠለፋ” እንዲሁም “ማሰቃየት እና ኢ-ሰብአዊ አያያዝ”፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለሰብአዊ መብቶች ትግበራ “ዋና ዋና ስጋቶች” እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተነበየ። ኮሚሽኑ በነጻ ሚዲያ እና በጋዜጠኞች ላይ “እየጨመረ መጥቷል” ያለውን “ገደብ” እና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ...
ዕድሜ ጠገቡ “ሲኒማ አምፒር” እና ሌሎች በቅርስ ተመዝግበው የነበሩ የፒያሳ ህንጻዎች ፈረሱ
በአዲስ አበባ ከተማ፣ ፒያሳ አካባቢ የሚገኙ እና ዕድሜያቸው ከ70 እስከ 100 ዓመት የሚጠጉ በቅርስነት የተመዘገቡ ህንጻዎች ፈረሱ። የፌደራል የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን በበኩሉ “ሲኒማ አምፒርን” ጨምሮ የፈረሱት ህንጻዎች “የቅርስ መመዘኛ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አይደሉም” ብሏል።
በመዲናይቱ አራዳ ክፍለ ከተማ ከፈረሱ ህንጻዎች መካከል ሸዋ ሆቴል፣ በስተኋላ ላይ ወደ ሄርሞን ሆቴል የተለወጠው...
በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ውስጥ “የግዳጅ አፈሳ መጀመሩን” የዓይን እማኞች ተናገሩ
በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ከተማ የጸጥታ ኃይሎች “የወጣቶች አፈሳ” ማካሄድ መጀመራቸውን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በመቐለ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ምድቦቻቸው እንዲመለሱ ጥሪ ሲደረግ የነበረ ቢሆንም፤ ዛሬ የታዩ እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሲካሄድ የቆየው አፈሳ ወደ ክልሉ ዋና ከተማ በይፋ መድረሱን እንደሚጠቁም ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የመረጃ ምንጮች አስረድተዋል።
በከተማው...
ህወሓት ከፌደራል መንግስት ሊደራደር የሚችለው “በሶስተኛ ሀገር” እንደሆነ የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጥቆማ ሰጡ
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፌደራል መንግስት ጋር የሚደራደር ከሆነ በአዲስ አበባ ከተማ ሳይሆን “በሌላ ሶስተኛ ሀገር” እንደሚሆን ለአሜሪካ ማሳወቁን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ተናገሩ። የአሜሪካ መንግስት “ቪዛ መከልከል ይቅር እና ሌላ ቢያደርግም”፤ “የትግራይ ህዝብ ህልውናን ለማረጋገጥ” ህወሓት “እስከ መጨረሻ እንደሚታገል” ኃላፊዋ ገልጸዋል።
“ሞንጆሪኖ” በሚለው የቅጽል ስማቸው ይበልጡኑ...
በትግራይ ክልል ካለው የግዳጅ አፈሳ ያመለጡ የዓይን እማኞች “እስር”፣ “ድብደባ” እና “ግድያ” ጭምር እየተፈጸመ...
የአዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆነው የ27 ዓመቱ ወጣት ጎይቶም ገብረስላሴ*፤ ከመቐለ እና ከመኖሪያ ከተማው የሚገዛቸውን ቡና እና በርበሬ ወደ ዛላንበሳ ከተማ እየወሰደ በመሸጥ የሚተዳደር ነው። ጎይቶም በትግራይ ክልል እና በኤርትራ ድንበር ወደምትገኘው ዛላንበሳ በሳምንት ሁለት ጊዜ እየተመላለሰ የንግድ ስራውን ሲያከናወን፤ ከዚህ ቀደም የከፋ ችግር አልገጠመውም።
በዚሁ ከተማ በሚገኝ ሻይ ቤት ውስጥ...
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 30...
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ግልገል በለስ ከተማ በመጓዝ ላይ በነበሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ትላንት ማክሰኞ ጠዋት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን የዓይን እማኞች እና የአካባቢው የፓርላማ ተወካይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የትላንቱን ጥቃት በተመለከተ መረጃ እንደደረሰው የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፤...
በጋምቤላ ክልል የጸጥታ መደፍረስ “ተሳትፎ ነበራቸው” የተባሉ 62 የፖሊስ አባላት ጉዳይ በህግ እየታየ መሆኑ...
በጋምቤላ ክልል ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ወቅት “በጥፋት ድርጊቶች ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸው ተረጋግጧል” ከተባሉ 272 የፖሊስ አባላት ውስጥ የ62ቱ ጉዳይ በህግ እየታየ መሆኑን አንድ የክልሉ ከፍተኛ ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ከዚህ ክስተት ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ 642 የፖሊስ እና የአድማ ብተና አባላትን ከስራ ማሰናበቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ በክልሉ ፖሊሶች...
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተዋጊዎች “የጦር ወንጀሎች” ሊሆኑ የሚችሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል...
በኦሮሚያ ክልል ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ግጭት ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፤ “የጦር ወንጀሎች” ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸሙን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። ሰራዊቱ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ “በቡድን አስገድዶ መድፈር” የደረሰ ጾታዊ ጥቃት፣ “የወሲብ ባርነት”፣ “ከህግ ውጭ ግድያ”፤ “ስቅየት” እና “የሲቪል ንብረት ውድመት”...
በጦርነት ስጋት ከትግራይ ክልል ወጣቶች እየሸሹ ነው
የመቐለ ከተማ ነዋሪው እዮብ* እና ቤተሰቦቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚመለከቷቸውና የሚሰሟቸው ወሬዎች፤ በልባቸው ውስጥ አንድ “ትልቅ ስጋት” ዳግም እንዲያንሰራራ አድርጓል። “ዳግም ጦርነት ሊጀመር ይችላል” የሚለው ስጋት በቤታቸው ውስጥ ጥላውን አጥልቷል።
ስጋታቸውን ይበልጥ ያገነነው፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወላጅ አባታቸው ለሕክምና ክትትል ወደ አዲስ አበባ ካቀኑ በኋላ ለመመለስ በሚሰናዱበት ወቅት...
ፌስታልን የሚተኩ ምርቶች እጥረት እና መወደድ ሸማቾች እና ነጋዴዎችን አስቸግሯል
ገነት ተስፋሁን በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፊጋ አካባቢ በግለሰብ ቤት ተቀጥራ የምትሠራ ወጣት ናት። ለሳምንት ፍጆታ የሚውል አትክልት እንድትገዛ ባለፈው እሁድ ረፋድ ላይ በአካባቢው አደባባይ ዙሪያ ወደሚገኘው “የእሁድ ገበያ” ትላካለች። የእቃ መያዣ ሳትይዝ ከቤት የወጣችው ገነት፤ ከረጢት መሰል ነገር ወደ ወደሚሸጡ ነጋዴዎች ተጠግታ ዋጋውን ስትጠይቅ የተሰጣት ምላሽ...
ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ “አዲስ ግጭቶች” “በፍጹም” ማየት እንደማትፈልግ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ “አዲስ ግጭቶች” “በፍጹም” ማየት እንደማትፈልግ እና በቀጠናው “ስቃይ ውስጥ በሚገኙ” ሰዎች ላይ “አዲስ ህመም” መጨመር እንደማይገባ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ ቀንድ የውጭ ኃይሎች “የመፋለሚያ ሜዳ” ሊሆን እንደማይገባም አሳስበዋል።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ማሳሰቢያውን የሰጡት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።...
የምርጫ ቦርድ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት በሰባት ፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሞ ቀረበበት
በመጪው ሀገር አቀፍ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎችን ለመመዝገብ የተዘጋጀው የዲጂታል ስርዓት፤ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “ከፉክክር ሜዳው በማውጣት ህዝብን አማራጭ አሳጥቶ ለመግዛት የታሰበ የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚል ነቀፋ ቀረበበት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ የምርጫ ሂደቱን “ለመጉዳት” በመስሪያ ቤቱ “ሆን ተብሎ የሚደረግ ተግባር የለም” ሲል አስተባብሏል።
ዛሬ አርብ ጥር 15፤ 2018...
የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ደህንነትን የተመለከተው የአዋጅ ማሻሻያ ምን ለውጦችን ይዟል?
ከ20 ዓመት በላይ በሥራ ላይ የቆየውን “የኢትዮጵያ አቪዬሽን ደህንነት አዋጅ” የሚያሻሻል የአዋጅ ረቂቅ፤ ትላንት ሐሙስ ጥር 14፣ 2018 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቀርቧል። የአዋጅ ረቂቁ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው፤ ውይይት ሳይካሄድበት እና አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ሳይቀርብበት ነው።
የህግ ረቂቁ በነባሩ አዋጅ ውስጥ ያልተካተቱ አዳዲስ...
“ከእያንዳንዱ ግጭት ዕድል ማውጣት ነው የሚጠበቅብን” – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ያሉ “መናጦች” እና “መታወኮችን” ባትፈልግም፤ ከእያንዳንዱ ግጭት “ዕድል ፈልቅቃ ማውጣት” እንደሚጠበቅባት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ዓለም ባልተናጠችበት ወቅት “ጥቅም አግኝተን፣ ስትናጥ እንደምንጎዳ ከእነሱ በላይ መጨነቅ የለብንም” ሲሉም ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በተሰኘ ኮንፍረንስ ላይ ከታደሙ ተሳታፊዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት...
የአዲስ አበባ አቅመ ደካሞች ስለ በዓል እና ኑሮ ውድነት ምን ይላሉ?
መብራት አልነበረም። በተንቀሳቃሽ ስልክ መብራት ወደ ቤቷ እየመራችን እንድንገባ ጋበዘችን። ‘ሁሉን አቀፍ’ የሆነች አንድ ክፍል ቤቷ ውስጥ፣ ሰፊውን ቦታ የያዘው አልጋ ነው። የልብስ ሳጥን፣ የምግብ ማብሰያ የተወሰኑ ቁሳቁሶች፣ እድሜ የጠገበ መሆኑ የሚያስታውቅ ተካፋች አጠር ያለ መደርደሪያ እና ከላዩ ባለው የግድግዳ ማዕዘን ቁልቁል የሚወርዱ፣ ጭስ ንጣቱን ሊጋርድ በሚታገለው መጋረጃ የተሸፈኑ የቅዱሳን...













































