ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ምርጫ የሚጠቀምበትን ምልክት እና ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ

ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ለመጪው ምርጫ ያዘጋጀው ማኒፌስቶ በዋናነት ትኩረት ያደረገው፤ “በመግባባት፣ በመፍታት፣ በማስፋት እና በመገንባት” ላይ መሆኑን መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ። የምርጫ ማኒፌስቶዉ ዋነኛ እሳቤ “ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር መትጋት” እንደሆነም ገልጸዋል። 

አቶ አደም ይህን የገለጹት፤ የሰባተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ባደረገበት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 3፤ 2018 በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ ከፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዱ የሆኑት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ እና ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የፓርቲው የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን አመራሮች በታደሙበት በዚህ መድረክ፤ ገዢው ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱ “የስንዴ ነዶ” መሆኑን ይፋ አድርጓል። ፓርቲው በባለፈው ምርጫ የተጠቀመበት ምልክት አምፖል እንደነበር ይታወሳል።

በስድስተኛው ዙር ምርጫ ወቅት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የሚያቀርቡበት እና የሚያስወስኑበት ጊዜ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ተካትቶ ነበር። ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ይፋ የተደረገው የዘንድሮው ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ግን ይህ ተግባር አልተካተተም።  

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethioelections.com/ብልጽግና-ፓርቲ-በመጪው-ምርጫ-የሚጠቀምበ/