ሚዲያ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአምስት ዓመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ አዲስ ዋና ዳይሬክተር ሊሾምለት ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀን በዕጩነት አቀረቡ። ላለፉት 23 ዓመታት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እና የመንግስት ተቋማት የሰሩት የወ/ሮ ሐይማኖት ሹመት፤ ነገ ማክሰኞ ታህሳስ 28፤ 2018 በሚካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን፤ መገናኛ ብዙኃን ተግባራቸውን በሕግ መሰረት...
መረጃ በሚከለክሉ ኃላፊዎች ላይ በአዋጅ የሚጣል ቅጣት ከ150 ሺህ ብር በላይ እንዲሆን ጥያቄ ቀረበ
መረጃ በሚከለክሉ ኃላፊዎች ላይ በመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ የተቀመጠው የቅጣት መጠን፤ ከ20 ሺህ ወደ 150 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከፍ እንዲል የኢትዮጵያ ብዙሃን መገናኛ ምክር ቤት ጠየቀ። መረጃዎችን በሰነድ መስጠት ሳይቻል ሲቀር፤ ኃላፊዎች በቃለ መጠይቅ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲሰጡ የሚያስገድድ አንቀጽ በአዋጁ ላይ መስፈር እንዳለበትም ምክር ቤቱ አሳስቧል።
ምክር...
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዋና አዘጋጅ ከዓለም የፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማት ተሸላሚዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ
ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” መስራቾች አንዱ የሆነው ተስፋለም ወልደየስ፤ ዓለም አቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት (IPI) እና ዓለም አቀፍ ሚዲያ ሰፖርት (IMS) የተባሉ ሁለት ተቋማት በትብብር ለሚሰጡት የዓለም ፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማት ተመረጠ። የእዚህን ዓመት ሽልማት እንዲቀበሉ የተመረጡት ተስፋለምን ጨምሮ ሰባት ጋዜጠኞች እና አርታዒያን ናቸው።
ዓለም አቀፉ ሽልማት ለሚዲያ ነጻነት ወይም ያልተገደበ የዜና እና...
Addis Ababa Cassation Bench upholds journalist Tesfalem Waldyes’ bail rights, orders police for his...
The Cassation Bench of Addis Ababa’s City Administration Court issued a ruling today regarding the admissibility of the police's appeal against the city’s appellate court decision on the bail rights of journalist Tesfalem Waldyes, the founder and editor-in-chief of the "Ethiopia Insider" online media outlet.
The Cassation Bench ruled that...
የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችሎት የጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት እንዲከበር አዘዘ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የዋስትና መብት ላይ ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ላይ ውሳኔ አስተላለፏል። የሰበር ሰሚ ችሎቱ የፖሊስን ማመልከቻ ጭብጥ ከመመልከቱ በፊት የቀረበለት ጉዳይ “ይግባኝ ያስቀርባል” ወይስ “አያስቀርብም” የሚለውን ዛሬ ጠዋት መርምሯል። በዚህም ሰበር ሰሚ ችሎቱ ባሳለፈው ውሳኔ...
Ethiopia Insider Editor-in-Chief Tesfalem Waldyes remains in custody despite being granted bail by court.
The Addis Ababa City Court of Appeal today, June 11, 2025, upheld the bail granted to Tesfalem Waldyes, founder and editor-in-chief of the “Ethiopia Insider” online media outlet. However, Tesfalem Waldyes has not been released as of the time of this statement, as the investigating police decided to appeal...
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስን በተመለከተ ከሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ – ሰኔ 4
የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 4 ቀን፤ 2017 የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በሥር ፍርድ ቤት የተወሰነለትን የዋስትና መብት አጽንቷል። ይሁንና መርማሪ ፖሊስ ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በመጠየቁ ተስፋለም ወልደየስ ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ሰዓት ድረስ ከእስር አልተፈታም። በአዲስ አበባ ከተማ...
Statement from Haq Media and Communication regarding the arrest of journalist Tesfalem Waldyes
Tesfalem Waldyes, the founder and editor-in-chief of Ethiopia Insider, an online media outlet managed by Haq Media and Communication, was arrested by security forces on Sunday, June 8, 2025. Haq Media and Communications has learned that he was taken into custody by plainclothed officers at the Ghion Hotel in...
የጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ መታሰርን በተመለከተ ከሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ
በሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥር የሚተዳደረው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እሁድ ሰኔ 1 ቀን፤ 2017 በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሏል። በአዲስ አበባ ከሚገኘው ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋለው ተስፋለም ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ...
በኢትዮጵያ በጋዜጠኞች ላይ ስለሚፈጸመው ተደጋጋሚ እስር ሲፒጄ ምን አለ?
በኢትዮጵያ ከመጋቢት ወር አጋማሽ እስከ ሚያዝያ ወር አጋማሽ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ 14 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሰራተኞች ለእስር ተዳርገው እንደነበር ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) አስታወቀ። ከታሰሩት ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች ውስጥ ሁለቱ አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ሲፒጄ ገልጿል።
ሲፔጄ ይህን የገለጸው፤ በየሀገራቱ ያሉ ጋዜጠኞችን...
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን እና ሶስት የጣቢያው ሰራተኞች በጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ተከሰሱ
በተስፋለም ወልደየስ
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን፣ እህት ኩባንያው እና ሶስት የጣቢያው ሰራተኞች የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል ክስ ቀረበባቸው። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበው በዚህ የክስ መዝገብ ክስ፤ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ፣ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን “ሀሰተኛ ታሪኳ ተሰራጭቷል” የተባለችው ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች በሽብር ወንጀል ተከስሰዋል።
በአጠቃላይ 16 ተከሳሾች የተካተቱበትን የክስ መዝገብ፤...
በኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት አሁንም “በከፍተኛ ጫና” ውስጥ እንደሆነ 14 ሀገራት በጋራ ባወጡት መግለጫ...
ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የ14 ሀገራት ኤምባሲዎች፤ በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ላይ ያለው “ከፍተኛ ጫና” መቀጠሉ እንደሚያሳስባቸው ገለጹ። በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ተልዕኮ በበኩሉ የፕሬስ ነጻነት አለመኖር “መረጃ የማግኘት መብትን እና የመተቸት ነጻነትን ያጓድላል” ብሏል።
ኤምባሲዎቹ እና የአውሮፓ ህብረት ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት በመላው ዓለም የሚከበረውን የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን...
ፖሊስ በአራት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች ላይ የጠየቀው የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ተፈቀደለት
⚫ በተጨማሪ አራት የጣቢያው ሰራተኞች ላይ የቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ለነገ ተቀጥሯል
በቤርሳቤህ ገብረ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ ጠርጥሬያቸዋለሁ” ባላቸው አራት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ። ባለፈው አርብ ፍርድ ቤት ከቀረቡ የጣቢያው ሰራተኞች መካከል፤ የካሜራ ባለሙያ የሆነው አቶ ቶማስ ደመቀ...
አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች “በሽብር ወንጀል” ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
በቤርሳቤህ ገብረ
የፌደራል ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ” ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞችን በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት አቀረበ። ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የፌደራል ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮውን የጠየቀው፤ በስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ስራ...
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አዲስ ዋና ዳይሬክተር ሊሾምለት ነው
በተስፋለም ወልደየስ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካሉት ሰባት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ሳምሶን መኮንን፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ በዕጩነት ቀረቡ። የአዲሱ ዋና ዳይሬክተር ሹመት ነገ ማክሰኞ ጥር 6፤ 2017 በሚካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዋና ዳይሬክተሩን ሹመት እንዲያጸድቅ፤ ጥያቄውን ያቀረቡት...












































