ምርጫ 2018

ኢዜማ በትምህርት ሚኒስቴር ባገኘሁት ኃላፊነት “ለምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቅሙኝን ሥራዎች ሠርቻለሁ” አለ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፤ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ለምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቅመውን ሥራ መሥራቱን አስታውቀ። የፓርቲው መሪ የትምህርት ሚኒስቴርን ለመምራት ባገኙት ዕድል፤ የፓርቲውን የትምህርት ፖሊሲ “ማስፈጸማቸውን” ገልጿል፡፡ ፓርቲው ይህን ያለው፤ ሰባተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ ዛሬ ታኅሣሥ 7፤ 2018 ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው። ኢዜማ በዚሁ መግለጫው፤ በዝምታ ውስጥ ያለው ሰፊው ማኅበረሰብ፣ ከምርጫ 2013 ልምድ በመውሰድ “የተለያዩ ኃሳቦች የሚንጸባረቁባቸው ምክር ቤቶች”...

የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወነው ከጥር 1 ጀምሮ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ መሆኑን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ሆኖ መጽደቁን አስታወቀ። ቦርዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ባደረገው የጸደቀ...

የኢትዮጵያ መንግስት በምርጫ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ “አፋጣኝ” እና “ተጨባጭ” እርምጃዎችን እንዲወስድ ዘጠኝ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ 

ስለመጪው ምርጫ ሂደትም ሆነ የጊዜ ሰሌዳን የተመለከተ ውይይት ከመደረጉ አስቀድሞ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰባት መሰረታዊ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ “አፋጣኝ” እና “ተጨባጭ” እርምጃዎችን እንዲወስድ ዘጠኝ የተቃዋሚ...

በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ያሉ የጸጥታ ሁኔታዎችን መከታተል የሚያስችል “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት” ሊዘረጋ መሆኑን ምርጫ...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ያሉ የጸጥታ ሁኔታዎችን የሚከታተልበት “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት” (early warning system) ለመዘርጋት ጥናት እያደረገ መሆኑን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አስታወቁ። ቦርዱ ባለፈው ሳምንት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባካሄደው ስብሰባ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ስጋቶች መንጸባረቃቸውን የገለጹት ዋና ሰብሳቢዋ፤ ሆኖም “ምርጫው ይራዘማል የሚል ነገር...

ምርጫ ቦርድ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በግንቦት 24 ለማካሄድ ምክረ ሃሳብ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24፤ 2018 ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቀረበ። ቦርዱ በምርጫው የሚገኘውን ውጤት ይፋ ለማድረግ፤ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ያስቀመጠው ዕለት ሰኔ 3፤ 2018 ነው። ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫውን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ለውይይት ያቀረበው፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጥቅምት 10፤ 2018...

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገራዊ ምርጫ ዘንድሮ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጡ

የኢትዮጵያ መንግስት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጠ። የመንግስትን ማረጋገጫ ዛሬ ሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ላይ በይፋ ያሳወቁት፤ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ናቸው።  ታዬ በህዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የስራ ዘመን መክፈቻ ላይ ባደረጉት በዚሁ ንግግር፤ የፌደራል መንግስትን ዓመታዊ እቅድ አቅርበዋል። የፕሬዝዳንቱ ንግግር አርባ...

መጪውን ሀገራዊ ምርጫ “ፈቃጅ” እና “አስቻይ” ሁኔታዎች ባሉባቸው አካባቢዎች ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ምርጫ...

በቤርሳቤህ ገብረ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ መጪው ሀገራዊ ምርጫ “ፈቃጅ” እና “አስቻይ” ሁኔታዎች ባሉባቸው የምርጫ ክልሎች እንደሚደረግ ገለጸ። በሀገሪቱ ያለው የጸጥታ ሁኔታ “በጣም ተለዋዋጭ በመሆኑ”፤ ምርጫው በሚቃረብበት ወቅት ሁኔታው “በዝርዝር” እና “በጥልቀት” የሚታይ መሆኑንም አስታውቋል።  ቦርዱ ይህንን ያስታወቀው፤ የሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 25፤...