በህገ ወጥ የነዳጅ ንግድ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎች እንዲወረሱ ታዘዘ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ ነዳጅ ጭኖ ወደ ጎረቤት አገራት የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ እንዲወረስ መታዘዙን ለፓርላማ አባላት ተናገሩ። እርምጃው የሚወሰደው ህገ ወጥ የነዳጅ ንግድን ለመከላከል በሚል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። 

የኢትዮጵያ መንግስት “ላለፉት ጥቂት አመታት ነዳጅ ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ደጉሟል” ያሉት አብይ፤ “ኢትዮጵያ ለአካባቢው አገራት ነዳጅ የምታቀርብ አገር ሆናለች” ሲሉ ህገ ወጥ ንግድ ችግር መፍጠሩን አስረድተዋል። ለዚህም ነጋዴዎችን እና ፤የነዳጅ ዘይት ማመላለሻ ተሽከርካሪ ባለቤቶችን ከስሰዋል።

 “የሁሉም ክልል ሚሊሺያዎች፣ ልዩ ኃይሎች ፖሊሶች ነዳጅ ከኢትዮጵያ ጭኖ የሚወጣ ቦቴ ካገኛችሁ ነዳጁን ብቻ ሳይሆን ቦቴውን ጭምር በመውረስ እንድትተባበሩን” የሚል ጥሪም አቅርበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)