በሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥር የሚተዳደረው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ዛሬ አርብ ሰኔ 6 ቀን፤ 2017 ከእስር ተፈትቷል።
ተስፋለም በእስር ላይ በቆየባቸው ያለፉት ቀናት አስፈላጊውን ትብብር ላደረጋችሁ ጓደኞቹ፣ የሙያ አጋሮቹ እና የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ቤተሰቦች ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ምሥጋናውን ይገልጻል። ተስፋለም ወልደየስ ከእስር እንዲፈታ ጥሪ ላቀረባችሁ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ምሥጋናችን ላቅ ያለ ነው።






























