ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የስልጤ ዞን ተወካዮች 800 ቤት ለአካባቢው ካልገነቡ ህዝብ እንዳይመርጣቸው አሳሰቡ  

በስልጤ ዞን ከወረዳ እስከ ፓርላማ ገዢውን ፓርቲ ወክለው የተመረጡ ተወካዮች፤ በጥቂት ወራት ውስጥ እያንዳንዳቸው 10 ቤት ለህዝብ ካልገነቡ በመጪው ምርጫ የአካባቢው ሰው ድምጽ እንዳይሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳሰቡ። የፌደራል መንግስት 1.5 ሚሊዮን ቤቶች የግንባታ ዕቅድ፤ እንደ ስልጤ ዞን ባሉ አካባቢዎች በገጠር ኮሪደር ልማት የሚሰሩ ቤቶችን እንደሚያካትትም አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫ እና የቤት ግንባታ ያስተሳሰሩበትን አስተያየት የሰጡት፤ የዞኑን አመራሮች ጨምሮ ከከፍተኛ...

በትግራይ ክልል በሬክተር ስኬል 5.6 እና 5.3 የተለኩ የመሬት መንቀጥቀጦች ተከሰቱ

በትግራይ ክልል ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 1፤ 2018 ምሽት፤ ለሁለት ጊዜያት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ። ከምሽቱ 1፡01 ላይ የደረሰው ርዕደ...

“የሊዝ ህግ ተላልፈዋል” የተባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሶስት ቀናት ውስጥ 45 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው 

በአዲስ አበባ ከተማ “የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ለንግድ ስራ አውለዋል” የተባሉ ነዋሪዎች፤ በሶስት ቀናት ገደብ ውስጥ እስከ 45 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር”...

በአራት ክልሎች ባሉ መንገዶች ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች የሚደርሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች “አሳሳቢ” መሆናቸውን ኢሰመኮ...

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልሎች ባሉ መንገዶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች የሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት መብት “አደጋ ላይ መውደቁን” አስታወቀ። በእነዚሁ ክልሎች በሚጣሉ ኬላዎች፣ የመንገድ መዘጋት እርምጃዎች፣ የሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደቦች እና በመንገዶች ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች የሚደርሱ...

የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዋና አዘጋጅ ከዓለም የፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማት ተሸላሚዎች አንዱ ሆኖ ተመረጠ 

ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” መስራቾች አንዱ የሆነው ተስፋለም ወልደየስ፤ ዓለም አቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት (IPI) እና ዓለም አቀፍ ሚዲያ ሰፖርት (IMS) የተባሉ ሁለት ተቋማት በትብብር ለሚሰጡት የዓለም ፕሬስ ነጻነት ጀግና ሽልማት ተመረጠ። የእዚህን ዓመት ሽልማት እንዲቀበሉ የተመረጡት ተስፋለምን ጨምሮ ሰባት ጋዜጠኞች እና አርታዒያን ናቸው። ዓለም አቀፉ ሽልማት ለሚዲያ ነጻነት ወይም ያልተገደበ የዜና እና...

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባለሃብቶች በችግር ጊዜ “ወደ ዱባይ የሚሸሹ መሆን የለባቸውም” አሉ 

በኢትዮጵያ የሚሰሩ ባለሀብቶች በተግዳሮት ወቅት ከመንግስት እና ከህዝብ ጋር የሚቆሙ “ታማኞች” መሆን እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳሰቡ። በደህናው ጊዜ “ሀብት የሚያካብቱ” ባለሃብቶች፤ በችግር ጊዜ “ወደ ዱባይ የሚሸሹ መሆን የለባቸውም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። አብይ ይህን ያሉት ትላንት ማክሰኞ መስከረም 27፤ 2018 ለታማኝ ግብር ከፋዮች ሽልማት በሰጡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር...

በአውሮፓ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማደስ ያለመ ኮንፈረንስ በፓሪስ ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የሚፈስሰውን የአውሮፓ መዋዕለ ንዋይ ለማሳደግ ያለመ ኮንፍረንስ በፈረንሳይ ፓሪስ ሊካሄድ ነው። ከአንድ ወር በኋላ በሚካሄደው በዚህ ኮንፍረንስ ላይ ከ100 በላይ የአውሮፓ ኩባንያዎች ተወካዮች ይታደማሉ ተብሏል።  በመጪው ጥቅምት 24፤ 2018 የሚካሄደውን ይህን ኮንፍረንስ በጋራ ያዘጋጁት የፈረንሳይ ቢዝነስ ኮንፌዴሬሽን (Medef) እና የአውሮፓ ኮሚሽን ናቸው። የፈረንሳይ ቢዝነስ ኮንፌዴሬሽን 173...

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገራዊ ምርጫ ዘንድሮ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጡ

የኢትዮጵያ መንግስት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጠ። የመንግስትን ማረጋገጫ ዛሬ ሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ላይ በይፋ ያሳወቁት፤ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ናቸው።  ታዬ በህዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የስራ ዘመን መክፈቻ ላይ ባደረጉት በዚሁ ንግግር፤ የፌደራል መንግስትን ዓመታዊ እቅድ አቅርበዋል። የፕሬዝዳንቱ ንግግር አርባ...

የፓርላማው ያለፈው ዓመት ክራሞት እንዴት ነበር?

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘንድሮው ስራውን ዛሬ መስከረም 26፤ 2018 በይፋ ይጀምራል። የተመረጡበት ጊዜ ሊጠናቀቅ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ የቀራቸው የስድስተኛው ዙር የፓርላማ አባላት፤ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አቻዎቻቸው ጋር ሆነው የመጨረሻ የስራ ዘመናቸውን የመክፈቻ ስነ ስርዓት ዛሬ ከሰዓት በተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ይታደማሉ። በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት መሰረት ህጎችን የማውጣት፣ የአስቸኳይ...

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ በአዲስ መዋቅር ስር ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀች

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) ቢዘጋም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈጸሙ “የሁለትዮሽ የእርዳታ ስምምነቶች” በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስር በተዘረጋው አዲስ መዋር እንደሚቀጥሉ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ። ኤምባሲው ዋነኛ ናቸው ያላቸው የሰብአዊ እርዳታ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና የምግብ ዋስትና መርሃ ግብሮች በአዲሱ መዋቅር እንደሚቀጥሉ ዛሬው ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።  አሜሪካ በእነዚህ...

በሽፋን ምርመራ ወቅት “ከግድያ በስተቀር” የሚፈጸም ወንጀልን ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው አወዛጋቢ ድንጋጌ ተሰረዘ

በቤርሳቤህ ገብረ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን “በሽፋን ስር” ሆኖ የመመርመር ኃላፊነት የተሰጠው ሰው፤ “ከግድያ በስተቀር” የሚፈጽማቸውን የወንጀል ድርጊቶች ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው ድንጋጌ ተሰረዘ። ድንጋጌው የተሰረዘው አዋጁ “በሰፊው እንዲተረጎም ስለሚያደርግ” እና በአተገባበሩም ላይ “አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያስከትል ስለሆነ ነው” ተብሏል።  አወዛጋቢው ድንጋጌ ተካትቶ የነበረው፤ በወንጀል የተገኘ ንብረትን...

የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰረዙባቸው ተጨማሪ ምክንያቶችን የያዘ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ   

በግለሰቦች፣ በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል “ስጋት፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬን እና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈጽሟል” ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። ቦርዱ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን “ህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያደናቀፈ” የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የመውሰድ ስልጣንም በአዋጅ ማሻሻያው ተሰጥቶታል።  ላለፉት አምስት...

በትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ኤምባሲዎችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው “በፍጥነት” ሚናቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ...

የትግራይ ክልል “ወደ ጦርነት እንዳይገባ” የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች ሚናቸውን “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ። በትግራይ ውጊያ ከተጀመረ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 26፤ 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች...

የመንግስት ገቢን “በከፍተኛ ደረጃ” ማሳደግ “የሞት የሽረት ጉዳይ ነው” ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ  

በቤርሳቤህ ገብረ የፌደራል መንግስት የሚሰብሰበውን ገቢ በሚቀጥለው ዓመት “በከፍተኛ ደረጃ” ለማሳደግ ማቀዱ “የሞት የሽረት ጉዳይ ነው” ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። በኢትዮጵያ ያለውን የልማት ፍላጎት ከአሁን በኋላ ማሳካት የሚቻለው ገቢን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ፤ “አዲስ የልማት ጥያቄ ለመፍታት ብለን ከብሔራዊ ባንክ የምንበደርበት ሁኔታ አብቅቶለታል” ብለዋል።  የገንዘብ ሚኒስትሩ...

ለሀገር አቋራጭ የህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና ዳግም ሊሰጥ ነው 

በቤርሳቤህ ገብረ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለሀገር አቋራጭ የህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች የዳግም ብቃት ምዘና መስጠት በቅርቡ እንደሚጀምር አስታወቀ። ምዘናውን ተከትሎ የሚሰጠው የብቃት ማረጋገጫ፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩ የጨመረውን የትራፊክ አደጋ በመቀነስ ረገድ “መሰረታዊ ለውጥ ያመጣል” የሚል እምነት እንዳለው ሚኒስቴሩ ገልጿል።  ይህ የተገለጸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን...

የኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ...

ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ብቻ ሲካሄድ የቆየው የባንክ ስራ አገልግሎት፤ ከዛሬ ጀምሮ ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። በዘርፉ መሰማራት የሚፈልጉ የውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ከዛሬ ጀምሮ ማመልከቻዎቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ ማስገባት እንደሚችሉም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።  አቶ ማሞ ምህረቱ በገዢነት የሚመሩት ብሔራዊ ባንክ ይህን ያስታወቀው፤...

Journalist Tesfalem Waldyes Freed from Detention

Today, Friday, June 13, 2025, we are delighted to announce the release of journalist Tesfalem Waldyes, the esteemed founder and editor-in-chief of the online media outlet "Ethiopia Insider," managed by Haq Media and Communication. We thank Tesfalem’s friends, dedicated colleagues, and the entire "Ethiopia Insider" family for their unwavering support...

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ተፈታ

በሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥር የሚተዳደረው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ዛሬ አርብ ሰኔ 6 ቀን፤ 2017 ከእስር ተፈትቷል።  ተስፋለም በእስር ላይ በቆየባቸው ያለፉት ቀናት አስፈላጊውን ትብብር ላደረጋችሁ ጓደኞቹ፣ የሙያ አጋሮቹ እና የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ቤተሰቦች ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ምሥጋናውን ይገልጻል። ተስፋለም ወልደየስ ከእስር እንዲፈታ ጥሪ...