ሰሞነኛ ጉዳዮች

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተዋጊዎች “የጦር ወንጀሎች” ሊሆኑ የሚችሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ግጭት ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፤ “የጦር ወንጀሎች” ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸሙን  አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። ሰራዊቱ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ “በቡድን አስገድዶ መድፈር” የደረሰ ጾታዊ ጥቃት፣ “የወሲብ ባርነት”፣ “ከህግ ውጭ ግድያ”፤ “ስቅየት” እና “የሲቪል ንብረት ውድመት” መፈጸሙን ድርጅቱ ገልጿል።  ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል...

በጦርነት ስጋት ከትግራይ ክልል ወጣቶች እየሸሹ ነው

የመቐለ ከተማ ነዋሪው እዮብ* እና ቤተሰቦቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚመለከቷቸውና የሚሰሟቸው ወሬዎች፤ በልባቸው ውስጥ አንድ “ትልቅ ስጋት” ዳግም እንዲያንሰራራ አድርጓል። “ዳግም ጦርነት...

ፌስታልን የሚተኩ ምርቶች እጥረት እና መወደድ ሸማቾች እና ነጋዴዎችን አስቸግሯል  

ገነት ተስፋሁን በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፊጋ አካባቢ በግለሰብ ቤት ተቀጥራ የምትሠራ ወጣት ናት። ለሳምንት ፍጆታ የሚውል አትክልት እንድትገዛ ባለፈው እሁድ ረፋድ...

ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ “አዲስ ግጭቶች” “በፍጹም” ማየት እንደማትፈልግ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ “አዲስ ግጭቶች” “በፍጹም” ማየት እንደማትፈልግ እና በቀጠናው “ስቃይ ውስጥ በሚገኙ” ሰዎች ላይ “አዲስ ህመም” መጨመር እንደማይገባ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ ቀንድ የውጭ ኃይሎች “የመፋለሚያ ሜዳ” ሊሆን እንደማይገባም አሳስበዋል።  የቱርኩ ፕሬዝዳንት ማሳሰቢያውን የሰጡት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።...

የምርጫ ቦርድ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት በሰባት ፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሞ ቀረበበት

በመጪው ሀገር አቀፍ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎችን ለመመዝገብ የተዘጋጀው የዲጂታል ስርዓት፤ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “ከፉክክር ሜዳው በማውጣት ህዝብን አማራጭ አሳጥቶ ለመግዛት የታሰበ የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚል ነቀፋ ቀረበበት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ የምርጫ ሂደቱን “ለመጉዳት” በመስሪያ ቤቱ “ሆን ተብሎ የሚደረግ ተግባር የለም” ሲል አስተባብሏል። ዛሬ አርብ ጥር 15፤ 2018...

የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ደህንነትን የተመለከተው የአዋጅ ማሻሻያ ምን ለውጦችን ይዟል?

ከ20 ዓመት በላይ በሥራ ላይ የቆየውን “የኢትዮጵያ አቪዬሽን ደህንነት አዋጅ” የሚያሻሻል የአዋጅ ረቂቅ፤ ትላንት ሐሙስ ጥር 14፣ 2018 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቀርቧል። የአዋጅ ረቂቁ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው፤ ውይይት ሳይካሄድበት እና አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ሳይቀርብበት ነው።   የህግ ረቂቁ በነባሩ አዋጅ ውስጥ ያልተካተቱ አዳዲስ...

“ከእያንዳንዱ ግጭት ዕድል ማውጣት ነው የሚጠበቅብን” – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 

ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ያሉ “መናጦች” እና “መታወኮችን” ባትፈልግም፤ ከእያንዳንዱ ግጭት “ዕድል  ፈልቅቃ ማውጣት” እንደሚጠበቅባት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ዓለም ባልተናጠችበት ወቅት “ጥቅም አግኝተን፣ ስትናጥ እንደምንጎዳ ከእነሱ በላይ መጨነቅ የለብንም” ሲሉም ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በተሰኘ ኮንፍረንስ ላይ ከታደሙ ተሳታፊዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት...

የአዲስ አበባ አቅመ ደካሞች ስለ በዓል እና ኑሮ ውድነት ምን ይላሉ?

መብራት አልነበረም። በተንቀሳቃሽ ስልክ መብራት ወደ ቤቷ እየመራችን እንድንገባ ጋበዘችን። ‘ሁሉን አቀፍ’ የሆነች አንድ ክፍል ቤቷ ውስጥ፣ ሰፊውን ቦታ የያዘው አልጋ ነው። የልብስ ሳጥን፣ የምግብ ማብሰያ የተወሰኑ ቁሳቁሶች፣ እድሜ የጠገበ መሆኑ የሚያስታውቅ ተካፋች አጠር ያለ መደርደሪያ እና ከላዩ ባለው የግድግዳ ማዕዘን ቁልቁል የሚወርዱ፣ ጭስ ንጣቱን ሊጋርድ በሚታገለው መጋረጃ የተሸፈኑ የቅዱሳን...

በግጭት ውስጥ የሰነበተው የጋምቤላ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምን ይመስላል?

በጋምቤላ ክልል አንጻራዊ መረጋጋት መስፈኑን እና ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው “እየተመለሱ መሆናቸውን” የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው አካባቢያቸው ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሰ ቢሆንም ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ መሆናቸውን እና አልፎ አልፎ ምሽት ላይ የተኩስ ድምጾች እንደሚሰሙ ተናግረዋል። የክልሉ ዋና መቀመጫ በሆነችው ጋምቤላ...

ሶማሌላንድን በተመለከተ በፓርላማ ለቀረቡ ጥያቄዎች፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሳይሰጡ ቀሩ  

እስራኤል ለሶማሌላንድ ከሰጠችው የነጻ ሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና በኋላ ዛሬ የመጀመሪያውን ስብሰባ ያደረገው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የደረሰችው የመግባቢያ ስምምነት “የት ደረሰ?” የሚል ጥያቄ አነሳ። በመደበኛ ስብሰባው ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስም ሆነ ምክትሎቻቸው ከሶማሌላንድ ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።  ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የዛሬ ሁለት...

እስራኤል ለሶማሌላንድ የሀገርነት እውቅና መስጠቷ ለኢትዮጵያ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

እስራኤል ከትላንት በስቲያ አርብ ለራስ ገዝ አስተዳደሯ ሶማሌላንድ የሰጠችው የነጻ ሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና በኢትዮጵያ ላይ የሚኖረውን አንድምታ በተመለከተ ሁለት የፖለቲካ ምሁራን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ከአረቡ ዓለም ጋር ባላት ግንኙነት ዙሪያ በርካታ ጥናቶችን በማድረግ የሚታወቁት ፕሮፌሰር አደም ካሚል ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር...

እስራኤል ለሶማሌላንድ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ ማን ምን አለ?

ላለፉት 34 ዓመታት ራሷን ከሶማሊያ ነጥላ ነጻ እና ሉዓላዊ ሀገር አድርጋ የምትቆጥረው ሶማሌላንድ፤ ዛሬ ዓርብ ታኅሣሥ 17፤ 2018 የመጀመሪያውን ይፋዊ የሀገርነት እውቅና ከእስራኤል አግኝታለች። እስራኤል ለሶማሌላንድ የነጻ ሀገርነት እውቅና መስጠቷን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ከሶማሌላንዱ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ ጋር በሞባይል ስልክ የቪዲዮ...

የፌስታል ምርቶችን መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ የትግበራ ጊዜ እንዲራዘም ሱፐርማርኬቶች እና አምራቾች ጠየቁ

ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ምርቶችን (ፌስታል) ከአንድ ወር በኋላ መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ የትግበራ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ሱፐርማርኬቶች እና አምራቾች ጠየቁ። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በበኩሉ አዋጁ ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የተሰጠው የስድስት ወራት የሽግግር ጊዜ እንደማይራዘም ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቋል። በግንቦት 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ “የደረቅ...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴር እና ሶስት ክልሎች ከተፈናቃዮች የመብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ክስ...

“ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” የተሰኘ ድርጅት፤ ዓለም-አቀፋዊ እና ሕገ-መንግስታዊ “ግዴታቸውን እና ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት” “በተፈናቃዮች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲደርሱ አድርገዋል” ያላቸውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴር እና ሶስት ክልሎችን በፍርድ ቤት ከሰሰ። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመመልከት ለነገ አርብ ለታኀሣሥ 17፤ 2018 ቀጠሮ ሰጥቷል።ሀገር በቀል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የክስ...

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን የመስከረም የደመወዝ ጭማሪ እስካሁንም አለመፈጸሙን በመግለጽ ቅሬታ አቀረቡ 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን፤ በአዲሱ የደመወዝ ማስተካከያ ጭማሪ መሰረት “የመስከረም ወር ክፍያ አልተፈጸመልንም” ሲሉ በማህበራቸው አማካኝነት ቅሬታ አቀረቡ። የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በበኩሉ ችግሩ የተፈጠረው በመረጃ ክፍተት ምክንያት ለፌደራል መንግስት የተላከው የገንዘብ መጠን ጥያቄ ከሚፈለገው በማነሱ እንደሆነ ገልጾ፤ ይህንኑ ለመቅረፍ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል። ለመንግስት ሰራተኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ...

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ድንጋጤ እና ፍርሃት ያስከተለው ውሳኔ 

የአሜሪካዊቷ ሚኒስትር ክሪስቲ ኖም ውሳኔ በቦስተን ከተማ ለምትኖረው ኢትዮጵያዊቷ ነርስ *ሜላት ገብረ እግዚያብሔር “መርዶ” ሆኖባታል። የአሜሪካ ዲፓርትመንት ኦፍ ሆምላንድ ሴኪዩሪቲ (Department of Homeland Security) ሚኒስትር የሆኑት ክሪስቲ ከትላንት በስቲያ አርብ ያስተላለፉት ውሳኔ፤ እንደ እርሷ ሁሉ “ጊዜያዊ ከለላ” አግኝተው በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን አስደንግጧል።  የ54 ዓመቷ ሚኒስትር የአርብ ዕለት ውሳኔ፤ ሜላትን ጨምሮ...

በጋምቤላ ከተማ የሰዓት እላፊ እንዲታወጅ መንስኤ የሆነው ምንድነው? 

ብሔራዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ግጭቶች አሳሳቢ መሆናቸውን በተለያየ ጊዜ በሚያወጣቸው መግለጫዎች እና ሪፖርቶች ሲገልጽ ቆይቷል። የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ከሦስት ሳምንት በፊት በክልሉ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት፤ ይኸው ጉዳይ ተነስቶ ነበር።  የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ...

ከ15 እስከ 20 በመቶ ተፈታኞችን ለዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ ከተቻለ “በጣም ትልቅ” ውጤት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ...

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ከ15 እስከ 20 በመቶ ያሉትን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲያልፉ ማድረግ የሚቻል ከሆነ “በጣም ትልቅ” ውጤት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። አንድም ተማሪ ለዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ ካልቻሉ እና ጉዳት ከደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል 700 ያህሉ ተለይተው፤ “የክትትል” እና “እገዛ” ስራ ከአንድ ወር በኋላ...