የመንግስት ኃይሎች የላሊበላ ከተማን መቆጣጠራቸው ተገለጸ

የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሺያ እና ፋኖ የላሊበላ ከተማን እና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸውን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። ጥምር ኃይሎቹ የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር በግስጋሴ ላይ መሆናቸውን የኮሚዩኒኬሽን መስሪያ ቤቱ ዛሬ ረቡዕ ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። 

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ጠዋት በሰጠው መግለጫ፤ የመከላከያ ሰራዊት በጋሸና ግንባር በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠሩን ገልጾ ነበር። የኢትዮጵያ ሰራዊት ጋሸናን መቆጣጠሩ፤ በላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ወልዲያ እና ደሴ በአማጽያን ቁጥጥር ስር ያሉ አካባቢዎችን “በአጭር ጊዜ ለማጽዳት መንገዱን የተመቻቸ ያደርገዋል” ሲል የቦታውን ስትራቴጂካዊነት አመላክቷል።

የህወሓት ኃይሎች ታሪካዊቷን የላሊበላ ከተማ መቆጣጠራቸው የተነገረው በሐምሌ ወር መጨረሻ ነበር። አማጽያኑ “ስትራቴጂካዊ” እንደሆነች የሚነገርላትን ደሴን የተቆጣጠሩት ደግሞ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)