ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ተወሰደ 

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ግንቦት 12፤ 2015 ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ተመስገንን የወሰዱት በሁለት ፒክ አፕ ተጨነው የመጡ እና የፖሊስ ደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እስከ ምሽት ድረስ ከቅርብ ጓደኞቹ ጋር የነበረው ተመስገን፤ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በሚገባበት ወቅት፤ የግቢ ዙሪያው በጸጥታ ኃይሎች ተከብቦ ማግኘቱን የዓይን እማኞቹ ተናግረዋል። እንደ እማኞቹ እና ቤተሰቦቹ ገለጻ፤ ተመስገን የተወሰደበት ቦታ እስከ ምሽት አራት ሰዓት ድረስ ማወቅ አልተቻለም። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)