ምስላዊ መረጃ፦ ዛሬ የካቲት 22 ሊጀመር ቀን ተቆርጦለት የነበረውን የመራጮች ምዝገባ፤ ወደ ቀጣዩ ወር መጋቢት አጋማሽ መዛወሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ ለቀኑ መራዘም በምክንያትነት ከጠቀሳቸው ውስጥ የምርጫ ክልል ጽህፈት ቤቶችን ለመክፈት በክልል መንግስታት በኩል የታየው ዳተኝነት፣ የዕጩዎች ምዝገባ መራዘም እና የምርጫ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የገጠመው ተግዳሮት ይገኙባቸዋል። በተሻሻለው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 16 ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 15 ይካሄዳል ተብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Recent Posts
ወደ መቐለ ተጉዞ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን፤ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ያረፈው ለምንድን...
ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ወደ መቐለ በረራ ያደረገ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን፤ በአሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ በሚገኝ የኮሚኒኬሽን መሳሪያ ብልሽት ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ለማረፍ መገደዱን አንድ የአየር መንገዱ ኃላፊ እና መንገደኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር”...
በነዳጅ የሚሰሩ 1,200 አውቶብሶችን ወደ ጋዝ ተጠቃሚነት ለመቀየር 1.4 ቢሊዮን ብር በጀት ያስፈልጋል ተባለ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ፣ በነዳጅ የሚሰሩ 1,200 የህዝብ ማመለሻ አውቶብሶችን ሞተር፤ በኢትዮጵያ መመረት የጀመረውን የተፈጥሮ ጋዝ እንዲጠቀሙ ለመቀየር 1.4 ቢሊዮን ብር በጀት እንደሚያስፈልግ የከተማይቱ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ። በመዲናይቱ የሚገኙ አውቶብሶችን ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተጠቃሚነት የመቀየር...
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ለ64 የፓርላማ መቀመጫዎች ብቻውን ለምርጫ መቅረቡ ታወቀ
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ግንቦት መጨረሻ በሚደረገው ምርጫ፣ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 64 የምርጫ ክልሎች ብቻውን ለፓርላማ እንደሚወዳደር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላትንናው ዕለት ይፋ ያደረገው ሰነድ አመለከተ። ከእነዚህ የምርጫ ክልሎች ውስጥ አርባ ስድስቱ በኦሮሚያ፣ አስራ...
ከዘንድሮ መጠባበቂያ በጀት 205 ቢሊዮን ብር ገደማ የገንዘብ እጥረት ላጋጠማቸው አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ተሰጠ...
የፌደራል መንግስት ለዘንድሮው በጀት ዓመት ለመጠባበቂያነት ከያዘው 269 ቢሊዮን ብር ውስጥ 76 በመቶውን ያዋለው፤ የበጀት እጥረት ላጋጠማቸው የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ፕሮግራሞች እና ተቋማቱ በበጀት ዝግጅት ጊዜያት ላላካተቷቸው ስራዎች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት...
በ2012 ዓ.ም የተመረጠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት፤ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ክልሉን እንዲመሩ ሾመ
ከስድስት ዓመት በተካሄደው አወዛጋቢ ምርጫ የተመረጠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት፤ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 27፤ 2018 ባደረገው ስብስባ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን የክልሉ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ። በህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ ወደ ስራ እንዲመለስ የተደረገው ይኸው ምክር ቤት፤...



































