ምርጫ 2018

ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እና መራጮችን በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ ሊጀምር ነው

በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎች እና መራጮች በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ የሚችሉበት መተግበሪያ እና የድረ ገጽ አማራጭ ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የዲጂታል አማራጮቹ፤ በስድስት የሀገሪቱ ቋንቋዎች ምዝገባ ለማከናወን እንዲችሉ ተደርገው መዘጋጀታቸውም ተገልጿል። ምርጫ ቦርድ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 27፤ 2018 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት ይፋ ማድረጊያ ስነ-ሥርዓት ላይ ነው። የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓቱ...

በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ያገኘ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር፤ ለቀጣዩ ምርጫ 1,200 ገደማ ዕጩዎችን ማዘጋጀቱን አስታወቀ

“ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት” የተባለው የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ፤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅንጅት ምዝገባ ምስክር ወረቀት አገኘ። የቅንጅቱ አካላት የሆኑ አራት ፓርቲዎች፤ በመጪው ምርጫው...

ኢዜማ በትምህርት ሚኒስቴር ባገኘሁት ኃላፊነት “ለምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቅሙኝን ሥራዎች ሠርቻለሁ” አለ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፤ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ለምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቅመውን ሥራ መሥራቱን አስታውቀ። የፓርቲው መሪ የትምህርት ሚኒስቴርን ለመምራት ባገኙት ዕድል፤ የፓርቲውን የትምህርት ፖሊሲ...

የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወነው ከጥር 1 ጀምሮ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ መሆኑን ምርጫ ቦርድ...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ሆኖ መጽደቁን አስታወቀ። ቦርዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ባደረገው የጸደቀ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ፤ የምርጫ ውጤት በቦርዱ ደረጃ ይፋ የሚደረገው ሰኔ 4 ቀን እንደሆነ ገልጿል።ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 30፤ 2018 ይፋ የተደረገው የጊዜ ሰሌዳ፤ በረቂቅ ደረጃ ከነበረው...

የኢትዮጵያ መንግስት በምርጫ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ “አፋጣኝ” እና “ተጨባጭ” እርምጃዎችን እንዲወስድ ዘጠኝ ተቃዋሚ የፖለቲካ...

ስለመጪው ምርጫ ሂደትም ሆነ የጊዜ ሰሌዳን የተመለከተ ውይይት ከመደረጉ አስቀድሞ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰባት መሰረታዊ ቅደመ ሁኔታዎች ላይ “አፋጣኝ” እና “ተጨባጭ” እርምጃዎችን እንዲወስድ ዘጠኝ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የፓርቲዎች ስብስብ ጠየቁ። መንግስት እና ገዢው ፓርቲ ቅድመ ሁኔታዎቹን በማሟላት፤ ለሁሉም ወገኖች “ነጻ እና ፍትሃዊ የሆነ” የውድድር ምህዳር እንዲፈጥሩ ፓርቲዎቹ ጥሪ...

በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ያሉ የጸጥታ ሁኔታዎችን መከታተል የሚያስችል “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት” ሊዘረጋ መሆኑን ምርጫ...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ያሉ የጸጥታ ሁኔታዎችን የሚከታተልበት “የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት” (early warning system) ለመዘርጋት ጥናት እያደረገ መሆኑን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አስታወቁ። ቦርዱ ባለፈው ሳምንት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባካሄደው ስብሰባ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ ስጋቶች መንጸባረቃቸውን የገለጹት ዋና ሰብሳቢዋ፤ ሆኖም “ምርጫው ይራዘማል የሚል ነገር...

ምርጫ ቦርድ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በግንቦት 24 ለማካሄድ ምክረ ሃሳብ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24፤ 2018 ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቀረበ። ቦርዱ በምርጫው የሚገኘውን ውጤት ይፋ ለማድረግ፤ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ያስቀመጠው ዕለት ሰኔ 3፤ 2018 ነው። ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫውን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ለውይይት ያቀረበው፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጥቅምት 10፤ 2018...

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገራዊ ምርጫ ዘንድሮ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጡ

የኢትዮጵያ መንግስት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጠ። የመንግስትን ማረጋገጫ ዛሬ ሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ላይ በይፋ ያሳወቁት፤ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ናቸው።  ታዬ በህዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የስራ ዘመን መክፈቻ ላይ ባደረጉት በዚሁ ንግግር፤ የፌደራል መንግስትን ዓመታዊ እቅድ አቅርበዋል። የፕሬዝዳንቱ ንግግር አርባ...

መጪውን ሀገራዊ ምርጫ “ፈቃጅ” እና “አስቻይ” ሁኔታዎች ባሉባቸው አካባቢዎች ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ምርጫ...

በቤርሳቤህ ገብረ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ መጪው ሀገራዊ ምርጫ “ፈቃጅ” እና “አስቻይ” ሁኔታዎች ባሉባቸው የምርጫ ክልሎች እንደሚደረግ ገለጸ። በሀገሪቱ ያለው የጸጥታ ሁኔታ “በጣም ተለዋዋጭ በመሆኑ”፤ ምርጫው በሚቃረብበት ወቅት ሁኔታው “በዝርዝር” እና “በጥልቀት” የሚታይ መሆኑንም አስታውቋል።  ቦርዱ ይህንን ያስታወቀው፤ የሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 25፤...