የኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪ ክልሎች እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤቶች ካሏቸው መቀመጫዎች መካከል ከግማሽ በላይ ዕጩዎችን ያቀረበው ገዢው ብልጽግና ፓርቲ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው ሰነድ አመለከተ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ በተወዳዳሪ ዕጩ ብዛት በተቃዋሚዎች የተበለጠበት ብቸኛው ምክር ቤት ሆኗል።
“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ዝርዝር ሰነድ፤ ብልጽግና ፓርቲ ምርጫ ከማይካሄድበት ትግራይ ክልል በቀር፣ በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች መንግስት ለመመስረት በሚያስችል የዕጩ ብዛት ይወዳደራል።
በቦርዱ ሰነድ መሠረት በሲዳማ ክልል ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ክልላዊ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል የዕጩዎች ብዛት አቅርበዋል። ይህም ሲዳማን ከፍተኛ ፉክክር የሚጠበቅበት ክልል አድርጎታል።
ብልጽግና ፓርቲ በዕጩዎች ብዛት በሌሎች ፓርቲዎች በተበለጠበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 143 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚነቱን ይዟል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ካሉት 158 መቀመጫዎች ውስጥ ሌላኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ሕዳሴ 142 ዕጩዎችን በማቅረብ ተከትሏል። ገዢው ፓርቲ ለከተማይቱ ምክር ቤት ያቀረባቸው ዕጩዎች 134 ሲሆኑ፤ ኢዜማ በአንጻሩ በ106 ዕጩዎች ይወዳደራል። (ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethioelections.com/2026/05/17605/
































