ሰሞነኛ ጉዳዮች

ምርጫ ቦርድ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በግንቦት 24 ለማካሄድ ምክረ ሃሳብ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24፤ 2018 ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቀረበ። ቦርዱ በምርጫው የሚገኘውን ውጤት ይፋ ለማድረግ፤ በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ያስቀመጠው ዕለት ሰኔ 3፤ 2018 ነው። ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫውን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ ለውይይት ያቀረበው፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ጥቅምት 10፤ 2018 ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር ላይ ነበር። በአዲስ አበባው ስካይ...

በትንሹ 2 ዓመት ዘግይቶ 3 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ያስወጣው የመስኖ ፕሮጀክት 

በኦሮሚያ ክልል፣ ባሌ ዞን፣ ደሎ መና ወረዳ የሚገኘው የወልመል ወንዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክት፤ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ጥቅምት 8፤ 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ...

በአዲስ አበባ ዘንድሮ የሚጀመር አዲስ የኮሪደር ልማት እንደሌለ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ 

በአዲስ አበባ ከተማ በዚህ ዓመት የሚጀመር አዲስ ኮሪደር ልማት እንደማይኖር የከተማይቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የከተማይቱ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት ከኮሪደር ልማት ጎን ለጎን...

ሙሉ ንግግር፦ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ...

የተከበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ። የተከበሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ። የተከበራችሁ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት። ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች። ክቡራትና ክቡራን!  የኢፌዲሪ ህገ መንግስት በሚደነግገው መሰረት፤ የሁለቱ ምክር ቤቶች የስራ ዘመን መጀመርን በይፋ ለማብሰር በሚከናወነው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝቼ ንግግር ለማድረግ በመቻሌ ከፍ ያለ...

የፓርላማው ያለፈው ዓመት ክራሞት እንዴት ነበር?

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘንድሮው ስራውን ዛሬ መስከረም 26፤ 2018 በይፋ ይጀምራል። የተመረጡበት ጊዜ ሊጠናቀቅ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ የቀራቸው የስድስተኛው ዙር የፓርላማ አባላት፤ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አቻዎቻቸው ጋር ሆነው የመጨረሻ የስራ ዘመናቸውን የመክፈቻ ስነ ስርዓት ዛሬ ከሰዓት በተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ይታደማሉ። በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት መሰረት ህጎችን የማውጣት፣ የአስቸኳይ...

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሻሻለው ህገ መንግስት “ተፈጻሚ እንዳይሆን”፤ ለሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ...

 በቤርሳቤህ ገብረ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የዛሬ ሁለት ሳምንት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው ላይ ያጸደቀው የክልሉ ህገ መንግስት ማሻሻያ፤ “የኢፌዲሪን ህገ መንግስት የሚቃረን ነው” ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት “ተፈጻሚ እንዳይሆን” አቤቱታ አቀረቡ። የምክር ቤት አባላቱ አቤቱታቸውን ያቀረቡት ለፌደራል የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ነው። የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ፤...

በመሬት መንቀጥቀጥ “ከፍተኛ ጉዳት” የደረሰበት የከሰም ስኳር ፋብሪካ፤ ሰራተኞቹን በመጪዎቹ ወራት ሊያሰናብት ነው 

በቤርሳቤህ ገብረ ባለፉት ወራት በተደጋጋሚ በተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች “ከፍተኛ ጉዳት” የደረሰበት የከሰም ስኳር ፋብሪካ፤ ከአንድ ሺህ በላይ ሰራተኞቹን እስከ መጪው ግንቦት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ለማሰናበት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። የስኳር ፋብሪካው የሰራተኞች ማህበር በበኩሉ ሰራተኞቹ ሳይሰናብቱ ወደ ሌሎች ፋብሪካዎች እንዲበተኑ ለማድረግ ጥረት እያደረገ መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቋል። ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ በ250...

ለአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት የሚውለው ገንዘብ ምንጭ፤ የከተማይቱ “ግብር ከፋዮች” መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ...

በቤርሳቤህ ገብረ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በአንድ ጊዜ በርካታ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር የሚያወጣው ገንዘብ ምንጭ፤ በከተማይቱ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ አነገጋረ። የከተማይቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የበጀታችን ምንጩ ግብር ነው። የከተማይቱ ግብር ከፋዮች ናቸው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።  የከተማይቱ ምክር ቤት አባላት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተተገበረ የሚገኘውን የኮሪደር...

የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እና ስርጭት መዘግየት፤ ዘንድሮ በፓርላማ ማነጋገሩን ቀጥሏል

በቤርሳቤህ ገብረ የግብርና ሚኒስቴር ኃላፊዎች የሩብ፣ የመንፈቅ፣ የዘጠኝ ወር አሊያም የዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለማቅረብ ወደ ፓርላማ በሚመጡበት ጊዜ ሁልጊዜም ከአንድ ጉዳይ ጋር የተያያዙ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ይቀርቡላቸዋል። ጉዳዩ አብዛኛውን የሀገሪቱን ህዝብ ብዛት የሚወክለውን አርሶ አደር በቀጥታ የሚመለከተው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እና ስርጭት ነው። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትላንት ሰኞ ጥር...

የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አመራሮች ሹመት፤ የፓለቲካ ገለልተኝነትን “ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው” የሚል ትችት...

በቤርሳቤህ ገብረ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሹመታቸውን ያጸደቀላቸው የኢትዮጵያ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አመራሮች የአመራረጥ ሂደት፤ “ከፓለቲካ ገለልተኝነት” ነጻ መሆን የሚለውን መስፈርት “ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው” የሚል ትችት በፓርላማ አባል ቀረበበት። ተሿሚዎቹ ለፓርላማ የቀረቡት፤ የፖለቲካ ገለልተኝነትን ጨምሮ እያንዳንዱ ጉዳይ “በደንብ” እና “በዝርዝር” ታይቶ መሆኑን የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ...

በጠለምት ወረዳ በመሬት መንሸራተት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፤ እርዳታ እና ዘላቂ የሰፈራ ቦታ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ

በደምሰው ሽፈራው የአማራ እና የትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው ጠለምት ወረዳ በመሬት መንሸራተት የተፈናቀሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች፤ ከአራት ወራት በኋላም “በጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ በመገደዳቸው” ለችግር መጋለጣቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የአካባቢው ባለስልጣናት ለተፈናቃዮቹ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ቢያመቻቹም፤ በበጀት እጥረት ምክንያት ለግንባታ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ አለመቻላቸውን ገልጸዋል። ከሰሜን...

በወላይታ ሶዶ ነዳጅ ማደያዎች የማይገኘው ቤንዚን፤ በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ እንዴት እንደ ልብ ሊገኝ ቻለ?

በናሆም አየለ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ እና የርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ የሆነችው የወላይታ ሶዶ ከተማ፤ በሰባት በሮች እንግዶቿን ትቀበላለች። የህዝብ ትራንስፖርት እና የግል ተሽከርካሪዎችን የሚጠቀሙ ተጓዦች፤ በአረካ፣ ቦዲቲ፣ ኡምቦ እና ገሱባ ከተሞች አድርገው ወደ ወላይታ ሶዶ መግባት ይችላሉ። በጭዳ፣ ሆቢቻ፣ በዴሳ ከተሞች በኩል ያሉ መንገዶችን ለተጓዦች በአማራጭነት ያገለግላሉ።   ከአዲስ አበባ ከተማ 332...

ህወሓት አወዛጋቢውን 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመቐለ ከተማ ማካሄድ ጀመረ 

በተስፋለም ወልደየስ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በተለያዩ ወገኖች ተቃውሞ እና ትችት የተሰነዘረበትን የጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ስነ ስርዓት፤ ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 7፤ 2016 በመቐለ ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት አዳራሽ አካሄደ። ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደው ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸውን ረዳን ጨምሮ 14 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ባልተገኙበት ነው።   ህወሓት ከስድስት ዓመት በኋላ...

ምርጫ ቦርድ ለህወሓት የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ 

በተስፋለም ወልደየስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት “በልዩ ሁኔታ” መስጠቱን አስታወቀ። ሆኖም ቦርዱ ህወሓት ያቀረበለትን “የቀድሞውን ህልውና ወደነበረበት የመመለስ” ጥያቄ አለመቀበሉን አስታውቋል። ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ ይህን ያስታወቀው፤ የህወሓትን ህጋዊ እውቅና የማግኘት ጉዳይ በተመለከተ ዛሬ አርብ ነሐሴ 3፤ 2016 ባወጣው መግለጫ ነው።...

በድጋሚ እና ቀሪ ምርጫ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁለት የፓርላማ መቀመጫ አሸነፉ 

⚫ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዲስ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ውጤት ይፋ ተደርጓል      በሙሉጌታ በላይ በሰኔ ወር አጋማሽ በአራት ክልሎች በተካሄደው “ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ”፤ ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁለት የፓርላማ መቀመጫ አሸነፉ። በባለፈው ጠቅላላ ምርጫ ያልተደረገባቸውን አብዛኞቹን የክልል ምክር ቤት እና የፓርላማ መቀመጫዎች፤ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል። በአፋር፣...

በቤት ኪራይ ውድነት የተቸገሩ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፤ በተማሪዎች ዶርም “በጊዜያዊነት” እየኖሩ ነው

በሙሉጌታ በላይ በትግራይ ክልል በሚገኘው መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ የተወሰኑ መምህራን “ቤት ተከራይቶ መኖር እንደከበዳቸው” ለተቋሙ ማመልከታቸውን ተከትሎ፤ በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም “በጊዜያዊነት” እንዲቆዩ ተፈቅዶላቸው እየኖሩ መሆኑን ገለጹ። የዩኒቨርስቲው መምህራን በክልሉ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የ17 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መሆኑ፤ በአስር ሺህዎች የሚቆጠር ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከማችባችው አድርጓል።   በ1992 ዓ.ም በወጣ ደንብ የተቋቋመው...

የጊዜ ገደቡ ስላበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ የኦፌኮ፣ የኢዜማ እና የእናት ፓርቲ አመራሮች ምን አሉ?...

በሙሉጌታ በላይ በአማራ ክልል ለአስር ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መፍትሔ እንዳላመጣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና እናት ፓርቲ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። ሌላኛው ተቃዋሚ ፓርቲ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ግን አዋጁ በክልሉ “የተወሰኑ መረጋጋት እንዲኖር አድርጓል” ሲል አስታውቋል። ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነው የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ...

“በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ” የፖለቲካ ፓርቲ፤ ማመልከቻው በ15 ቀናት ውስጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ...

በተስፋለም ወልደየስ “በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ” የፖለቲካ ፓርቲ፤ “በልዩ ሁኔታ” ለመመዝገብ ማመልከቻ ባቀረበ “በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ምዝገባው እንዲፈጸም” የሚያደርግ አዋጅ በነገው ዕለት ለፓርላማ ቀርቦ ሊጸድቅ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ መልኩ የቀረበለትን ማመልከቻ ውድቅ የማድረግ አማራጭ በአዋጁ ባይሰጠውም፤ በፓርቲው ላይ ለሁለት ዓመታት “ክትትል እና ቁጥጥር” የማድረግ...