የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር
በትጥቅ ትግል እና በእስር ላይ ያሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን በምክክር ሂደት ለማሳተፍ የጀመረውን ጥረት...
በተስፋለም ወልደየስ
በተለያዩ ምክንያቶች ጫካ ገብተው ትጥቅ ትግል እያካሄዱ የሚገኙ፣ እስር ቤት ያሉ እንዲሁም ሀገራቸውን ለቅቀው የተሰደዱ የአማራ ክልል ተወላጆች፤ በሀገራዊ ምክክር እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ለመፍጠር የጀመረውን ጥረት “አጠናክሮ እንደሚቀጥል” የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ጥረቱን ከግብ ለማድረግ “የተለየ ትኩረትም ሰጥቶ” እንደሚሰራ ገልጿል።
ይህ የተገለጸው ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 2፤...
የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ሲያካሄዱት የቆየው የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተጠናቀቀ
የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ካለፈው እሁድ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲያካሄዱት የቆየው የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተጠናቀቀ። የማህበረሰብ ተወካዮቹ፤ በመጪዎቹ ቀናት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ የምክክር ሂደት የሚሳተፉ 270 ወኪሎቻቸውንም መርጠዋል።
በቁጥር ከ4,500 በላይ የሚሆኑት እነዚህ የማህበረሰብ ተወካዮች፤ በክልሉ ካሉ 263 ወረዳዎች የተመረጡ ናቸው። አስር የማህበረሰብ ክፍሎችን የወከሉት...
የአማራ ክልል የሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተጀመረ
በተስፋለም ወልደየስ
በመጪው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከአማራ ክልል የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት፤ ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 27፤ 2017 በባህርዳር ከተማ በይፋ ተጀመረ። የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ወክለው በባህርዳር ከተማ የተሰባሰቡ ከ4,500 በላይ ተሳታፊዎች፤ ክልሉን በመወከል በሀገር አቀፉ ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችን ይመርጣሉ።
በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ስቴዲየም በተካሄደው በዛሬው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የማህበረሰብ ክፍሎቹ...
የተወካዮች ምክር ቤት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ለአንድ ዓመት አራዘመ
በቤርሳቤህ ገብረ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 11፤ 2017 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ለአንድ አመት አራዘመ። የኮሚሽኑን የስራ ዘመን ለማራዘም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ፤ በሶስት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ በአብላጫ ጽምጽ ጸድቋል።
መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተፈጠሩ ልዩነቶች “ወሳኝ ምክንያቶችን የመለየት” እና ውይይቶች የሚካሄዱባቸውን ርዕሰ...
ፓርላማው በመጪው ማክሰኞ በሚያካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፤ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል
በቤርሳቤህ ገብረ
የሶስት አመት የስራ ዘመኑን እያገባደደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፤ አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን በመጪው ማክሰኞ በሚካሄድ አስቸኳይ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ሊያቀርብ ነው። በዚሁ ስብሰባ ላይ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ “የስራ ዘመን ይራዘማል” ተብሎ እንደሚጠበቅ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
በታህሳስ 2014 ዓ.ም የጸደቀው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን...
የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ለሀገር አቀፍ ምክክር እንዲቀርቡ የጠቆሟቸው አጀንዳዎች የትኞቹ ናቸው?
በናሆም አየለ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ማካሄድ የጀመረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል። በክልሉ ከሚገኙ 356 ወረዳዎች በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉት ተሳታፊዎች፤ ከትላንት ማክሰኞ ታህሳስ 8፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመጪው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ነው።
በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ የመሰብሰቢያ...
ከኦሮሚያ ክልል ለሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት ከነገ ጀምሮ ሊካሄድ ነው
በናሆም አየለ
ከኦሮሚያ ክልል በሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደት ከነገ ሰኞ ታህሳስ 7፤ 2017 ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ቀናት ሊካሄድ ነው። በዚሁ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ላይ ስምንት ሺህ የሚጠጉ የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎች እና የክልል ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በአዳማ ከተማ የሚካሄደው ይህ የአጀንዳ ማሰባሰብ...
በሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎች የማሰባሰብ ሂደት፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዛሬ ተጀመረ
በናሆም አየለ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረኛ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረኩን፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በወላይታ ሶዶ ከተማ በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀመረ። በዚሁ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ፤ በክልሉ ከሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ ቁጥራቸው ሁለት ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
የዛሬውን መርሃ ግብር የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ካሉት 11 ኮሚሽነሮች...
በምርጫ ቦርድ የታገዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በሀገራዊ የምክክር ሂደት ላይ መሳተፋቸው ይቀጥላል ተባለ
በናሆም አየለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ማናቸውንም ህጋዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ” ያገዳቸውን ፓርቲዎች፤ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ማሳተፉን እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ። ፓርቲዎቹ በመጪው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይም በተወካዮቻቸው በኩል እንዲሳተፉ እንደሚያደርግ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ይህን ያስታወቀው ከዛሬ ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚደረገውን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ አስመልክቶ፤ ትላንት እሁድ...
በክልሎች የሚደረገው የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ በመጪው ሳምንት ሊጀመር ነው
በናሆም አየለ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በክልሎች የሚያደርገውን የአጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ፤ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጀምር ገለጸ። የምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚካሄድባቸው፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሀረሪ ክልሎች እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ናቸው።
በሀገራዊ ምክክር ላይ “አጀንዳ ሊሆኑ ይገባሉ” የተባሉ ጉዳዮች የማሰባሰብ ሂደት በቅድሚያ የተካሄደው፤ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ነበር።...
በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አዲስ አበባን የወከሉ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች የምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከቡ
በናሆም አየለ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በመወከል በሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ሲሳተፉ የቆዩ ተወካዮች፤ በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ “ሊመከርባቸው ይገባሉ” ብለው የለዩአቸውን ጉዳዮች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ምክር ቤት አስረከቡ። ተወካዮቹ ለምክክር ካስያዟቸው አጀንዳዎች ውስጥ “የአዲስ አበባ ባለቤትነት እና አወቃቀር፣ የቋንቋ፣ የሰንደቅ አላማ እና...
የሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀመረ
በተስፋለም ወልደየስ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍን፤ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 21፤ 2016 በይፋ አስጀመረ። የአዲስ አበባው ምክክር፤ የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ ገና ላልተወሰነለት ለመጪው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ “ቁልፍ ሚና ይኖረዋል” ተብሎለታል። በታህሳስ 2014 ዓ.ም. በአዋጅ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ስራዎቹን ሲያከናወን...
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ምክክር ላይ በአጀንዳነት የሚቀርቡ ጉዳዮችን እንዲያዘጋጁ ተጠየቁ
በናሆም አየለ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በሀገራዊ ምክክር ላይ “አጀንዳ ሊሆኑ ይገባሉ” የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዲያዘጋጁ ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በደብዳቤ ጥሪ አቀረበ። የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሚያቀርቧቸው አጀንዳዎች ላይ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት እና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት የሚያካሄዱበትን ሁኔታ እንደሚመቻች ኮሚሽኑ አስታውቋል።
“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው እና ባለፈው ሳምንት ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተላከው ደብዳቤ፣ የኢትዮጵያ...
በሀገራዊ የምክክር ሂደት ላይ በአጀንዳ ግብዓት ማሰባሰብ የሚሳተፉ ተወካዮች መረጣ በ850 ወረዳዎች መጠናቀቁ ተገለጸ
በናሆም አየለ
በኢትዮጵያ ካሉ 1,300 ወረዳዎች መካከል በ850ዎቹ የምክክር አጀንዳዎች የሚለዩ ተወካዮች ምርጫ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ “ባጠሩ ሳምንታት” ውስጥ አጀንዳ የማሰባሰብ ስራውን ሊጀምር በመሆኑ፤ የወረዳ እንዲሁም የክልል ተወካዮች ከወከላቸው የማህበረሰብ ክፍል ጋር ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርቧል። የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ዛሬ አርብ መጋቢት 27፤ 2016...
የሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ሃሳቦችን የሚሰጡ ተወካዮችን ያስመረጡ ወረዳዎች ብዛት 327 መድረሱ ተገለጸ
በተስፋለም ወልደየስ
በኢትዮጵያ ካሉ ወረዳዎች መካከል 327 የሚሆኑት በሀገራዊ ምክክር ላይ የአጀንዳ ሃሳብ የሚሰጡ ተወካዮችን ሙሉ ለሙሉ መርጠው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። የአማራ እና የትግራይ ክልሎች “አሁን ባሉባቸው ወቅታዊ ሁኔታዎች” ምክንያት ተወካዮችን የሚመርጡ ተሳታፊዎችን እስካሁን ድረስ መለየት አለመጀመራቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።
የኮሚሽኑ ቃል አቃባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ዛሬ አርብ ታህሳስ...